ምክትል ከንቲባው ነጥብ ጥለው ወርደዋል። (በጋዜጠኛ ቆንጂት ተሾመ)

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

በሚሊኒየም አዳራሽ ለአርቲስትና ሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ለታማኝ በየነ በተዘጋጀው የክብር አቀባበል ላይ ንግግር ለማድረግ መድረክ ላይ የወጡት የአ.አ. ምክትል ከንቲባ አቶ ታከለ ኡማ “ጣይቱ ጣይቱ የሚል የሺዎች ድምጽ ቀልባቸውን ሳይገፈው አልቀረም የተዘጋጁበትን መልዕክት በአግባቡ ሳያስተላልፉ ቀርተዋል።

ታማኝን ደጋግመው “ውድ ወንድሜ ..” እያሉ ከመግለጽ ሌላ ለታዳሚው ልብ ጠብ የሚል መልዕክት አልተናገሩም።

ይዘው የመጡትን ንግግር እጃቸውን እያፍተለተሉ የራስ የመተማመናቸው ወርዶ ነበር የተናገሩት። ከመድረክ ሲወርዱም የሞቀ ጭብጨባ አላጀባቸውም። ወንበራቸው ላይ እንደተቀመጡም የግንባራቸውን ላብ ነበር የጠረጉት።

ህዝቡ በሶስት ፊደል በአንድ ቃል ብቻ የሰጣቸው የጣይቱ የቤት ስራ እንቅልፍ የሚያስተኛቸው አይመስልም።

Share.

About Author

Leave A Reply