“ምድረ ቀደምት” የሚለው አዲሱ የቱሪዝም ኢትዮጵያ መለዮ ሕብረተሰቡም ሆነ ቱሪስቶች አያውቁትም ተባለ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የቱሪዝም ኢትዮጵያ “ምድረ ቀደምት” የሚለው አዲሱ መለዮ በተፈለገው መጠን በኅብረተሰቡ ዘንድ እንዳልሰረጸ የኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅት አስታወቀ።

የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሌንሳ መኮንን ትናንት በተካሄደ የውይይት መድረክ ላይ እንዳስታወቁት የሀገሪቱ የቱሪዝም መለዮ ስያሜ ‹‹የ13 ወር ጸጋ›› የሚለው ከሦስት ዓመት በፊት ወደ ‹‹ምድረ ቀደምት›› መቀየሩ ይፋ ቢደረገም አዲሱን ስያሜ ኅብረተሰቡም ሆነ ቱሪስቶች እንዲያውቁት በሚያስችል ደረጃ አልተሠራም። ይህም በመሆኑ የቀደመው ስያሜው የሠራውንና መለዮ የሆነውን ያህል አዲሱ መለዮ ተጽዕኖ አለመፍጠሩን ገልጸዋል፡፡

‹‹ኢትዮጵያን በሚገባ ይገልጻታል›› የተባለው አዲሱ የቱሪዝም መለዮ ኢትዮጵያ የሁሉ ነገር መነሾ እንደሆነች የማስተዋወቅ አቅም እንዳለው ጠቁመው ድርጅቱ የማስተዋወቁን ሥራ በሚገባ ባለመሥራቱ መለዮው በሚጠበቀው ልክ እንዳይታወቅ አድርጎታል ብለዋል፡፡ ይህንን ችግር ለመቅረፍ አንዱ መንገድ አገራዊ የምክክር መድረክ ማዘጋጀት ሆኖ በቀጣይም ከሚመለከታቸው የባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች በመዞር እስከ ታችኛው የአገሪቱ መዋቅር ድረስ በመውረድ የማሳወቅ ሥራ እንደሚሠራ ተናግረዋል፡፡

የቱሪዝም ኢትዮጵያ የገበያ ልማት ቡድን መሪ አቶ ወልደገብርኤል በርሄ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ያላትን የቱሪዝም ሀብት በሚገባ ያልተጠቀመች አገር መሆኗን ገልጸዋል፡፡ አፍሪካ የዓለም አቀፍ ቱሪዝም ድርሻዋ እየተሻሻለ የመጣ ቢሆንም ካላት እምቅ የቱሪዝም አማራጮች አንጻር ዝቅተኛ መሆኑን በዓለም አቀፉ ቱሪዝም ድርጅት የተደረገ ጥናት እንደሚያመለክት ጠቅሰው ኢትዮጵያም ያላትን የቱሪዝም ሀብት በአግባቡ ባለመጠቀም እንደምትታወቅ አንስተዋል፡፡

ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ለትምህርት፣ ለሥራ እንዲሁም ለተለያዩ ጉዳዮች ከአገር አገር ሲዘዋወር መለዮን ጨምሮ አገሪቱ ውስጥ የሚገኙ የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎችን ማስተዋወቅ እንደሚገባውም ተናግረዋል። ድርጅቱም የተለያዩ ስልቶችን ነድፎ መለዮ

Share.

About Author

Leave A Reply