ም/ጠ/ሚ አቶ ደመቀ መኮንን በሴራሊዮን ጉብኝት እያደረጉ ነው

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በሴራሊዮን የሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራ ከፍተኛ የመንግሥት ልዑክ በሴራሊዮን መዲና ፍሪታውን በደረሰበት ወቅት በሃገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።

ጉብኝቱ በኢትዮጵያ እና በሴራሊዮን መካከል ሊኖር የሚገባውን የዲፕሎማሲ ግንኙነት እና የሁለትዮሽ ትብብር ለማጠናከር ያለመ ነው ተብሏል። ልዑኩ በሁለት ቀናት ቆይታው ከሴራልዮን መንግስት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር በሁለትዮሽ ግንኙነት እና ሁሉን አቀፍ ትብብር ዙሪያ ይመክራል፡፡

ምክክሩን ተከትሎም የጋራ መግባቢያ ሰነዶች እንደሚፈራረሙም ይጠበቃል። አቶ ደመቀ መኮንን ጉብኝቱን የሚያካሂዱት የሴራሊዮን ፕሬዝዳንት ጁልየስ ማዳቢዩ ባደረጉላቸው ግብዣ መሰረት መሆኑን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Share.

About Author

Leave A Reply