ሩሲያ ኢትዮጵያውያን የእግር ኳስ ደጋፊዎች ለዓለም ዋንጫው ያለ ቪዛ እንዲገቡ ፈቀደች

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ሩሲያ በሚቀጥለው ወር ለምታስተናግደው የዓለም ዋንጫ ኢትዮጵያውያን የእግር ኳስ ደጋፊዎች ያለ ቪዛ ወደ ሃገሯ እንዲገቡ ፈቀደች።

 

የዓለም ዋንጫን መታደም የሚፈልጉ ደጋፊዎች ህጋዊ ፓስፖርትና የደጋፊ መታወቂያ በመያዝ ያለ ቪዛ ወደ ሩሲያ በማምራት ውድድሩን መከታተል እንደሚችሉ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በላከው መግለጫ አስታውቋል።

በዚህም ውድድሩን በስፍራው በመገኘት መከታተል የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን የደጋፊ መታወቂያውን www.fan-id.ru በሚለው ድረ-ገጽ ላይ በመመዝገብ ማግኘት እንደሚችሉም ገልጿል።

የሩሲያው የዓለም ዋንጫ ከሰኔ 7 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ ለአንድ ወር የሚካሄድ ይሆናል።

ተሳታፊ ሃገራትም በውድድሩ የሚካፈለውን የመጨረሻ የቡድን ስብስባቸውን ይፋ እያደረጉ ይገኛል።

Share.

About Author

Leave A Reply