“ሰርቄ እንዳልበላ ስሜ ትልቅ ነው።” በኢትዬ ኤርትራ ጦርነት ምሽግ በመስበር ድፍን ኢትዬጵያን በደስታ ያስፈነደቀውና ያልተዘመረለት ጀግና መቶ አለቃ ቀሬ ደጉ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

“ሰርቄ እንዳልበላ ስሜ ትልቅ ነው። ለእናትና አባቴ አንድ ልጅ ስለነበርሁና ጎጃሜ በመሆኔ ለምኘና ሰርቄ መብላት አላለመዱኝም”–
በኢትዬ ኤርትራ ጦርነት ወቅት ምሽግ በመስበር ድፍን ኢትዬጵያን በደስታ ያስፈነደቀውና ደብረ ማርቆስን ያስጠራው ያልተዘመረለት ጀግና መቶ አለቃ ቀሬ ደጉ ፡፡

ይህንን ጀግና በርካታ ሚዲያዎች በተደጋጋሚ ፈልገውት አጠውታል፤እኔ እንደፈልገው ነግረውኝ በእግር በፈረስ አስፈልጌው ነበር፡፡ ግን ይህ ታሪክ ሰሪ በምስራቅ ጎጃም ዞን አስፈልጌ በማጣቴ ለሚዲያዎች እንዳላገኘሁት ነግሬ ውስጤ ቢያርም ዝም ከማለት ባለፈ አማራጭ አልነበረኝም፡፡

ዛሬ ጥዋት አንድ የደብረ ማርቆስ ከተማ ወጣት ነጋዴ ይህንን ያልተዘመረለት ጀግና እንዳገኘ በጥዋቱ ስልክ ደወለልኝ፡፡ ስልኬን ሳነሳው መቶ አለቃ ቀሬን አገኘሁት እባክህን ድረስልኝ አለኝ፡፡ እውነቱን ለመናገር ከ1 ኪሎ ሜትር በላይ ርቀት የሚወስድ ቢሆንም አምስት ደቂቃ እንኳ የፈጀብኝ አይመስለኝም፡፡
እንዳገኘሁት ተጠመጠምሁበት ግን ችግር አድክሞታል፡፡ ቀጥዬ ታሪኩን እንዲነግረኝ ስጠይቀው እጅግ ደስተኛ ነበር፡፡

መቶ አለቃ ቀሬ ደጉ የተወለደው በምስራቅ ጎጃም ዞን በአነደድ ወረዳ አምበር ከተማ ቢሆንም ያደገው እዚሁ ደብረ ማርቆስ ከተማ ቀበሌ 06 ነው፡፡
መቶ አለቃ ቀሬ ደጉ በ1990 ዓም ኢትዬጵያ በኤርትራ ስትወረር ሃገሩን ለመታደግ ወደ ውትድርና ገባ፡፡ ይህ ያልተዘመረለት ጀግና በወቅቱ ከአሁኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ስር ሆኖ ተዋግቷል፡፡ መቶ አለቃ ቀሬ በሙያው ከአንድ አመት በላይ ልምድ ባይኖረውም ጀግንነቱ የዘር ነውና በኢትዬ ኤርትራ ጦርነት ገዛ ገብረ ስላሴ ምሽግን በተሰጠው ተልእኮ መሰረት ከጓደኛው ሌላኛው ጎጃሜ የሜጫው ልጅ ዋሲሁን ገላ ጋር በመሆን ምሽግ ሰብሮ አገርን አስፈነደቀ፡፡ ሃገሩን ጎጃምን አኮራ፣ የበላይ ዘር አሰኘ፡፡

መቶ አለቃ ቀሬ አለም ቢያጨበጭብም የማእረግ እድገት አላገኘም፣
ይልቁንም ባልደረቦቹ ትኩር ጥምድ አድርገው ያዙት፡፡ አንተ የሻቢያ የዘር ሃረግ ኑሮብህ ከእነሱ መረጃ አግንተህ ነው እንጅ እኛ የ17 አመት ልምድ ያለን ሰዎች እያለን አንተ በምን ሚስጥር ጀብድ ልትሰራ ትችላለህ በሚል ህይወቴ ውጥንቅጡ እንዲወጣ አደረጉት ይላል፡፡

ይሁን እንጅ የተሸለ ቦታ ባለመሰጠቴ እያዘንሁ በመቀጠል በ1992 ዓም መጨረሻ በተቋሙ ወደ አካባቢ ጎጃም ሄጀ ወጣቱን እንዳነሳሳ፤ ሃገር እንዳትደፈር እንዲያደርግ፣ እንዳስተምር ተላክሁ፡፡ ጎጃም ስገባ ከአማኑኤል እስከ ደጀን ከተማ ያለው ወጣት ሰንደቅ አላማ ለብሶ እኔን ተሸክሞ ጨፈረ፡፡ ይህን ፍቅር ህዝብ አገር ማዳን እንዳለበት ባምንም በእኔ ላይ የሆነውን ሳስብ ከራሴ ጋር ተጣላሁ፡፡ አቋርጨ ወጣቱን ለማስተማር ትንሽ ቀን ስጡኝ ብዬ አመራሩን በመጠየቄ ስማቸውን መናገር የማልፈልጋቸው ሰዎች መውጫ መግቢያ አሳጡኝ፡፡ ዛቱብኝ፡፡

ተመልሸ ወደ መከላከያ ስሄድ ቀድሞ ተነግሮ ኖሯል፡፡ አንተ ሻቢያ መጣህ፤ ብለህ ብለህ ደግሞ ወደ መከላከያ ወጣት እንዲሄድ አልቀሰቅስም አልህ በሚል ጎንደር ሁለተኛ ጣቢያ ለረጅም ጊዜ ታሰርሁ፡፡ እራበኝ ብዬ ስጠይቅ አላማውም በርሃብ እንድትሞት ነው ይሉኛል፡፡ ማረጌን አንስተው ሽንት አስደፍተውኛል፡፡ ከሁለት ወር በኋላ ለቀቁኝ ፤ወደ መከላከያ ስሄድ ጎጃም ተወልጀ አንተ ሻቢያ ጥፋ አሉኝ፡፡
በዚህ ምክንያት ያለምንም ነገር ተመልሸ ወደ ጎጃም ተመለስሁ፡፡ እዚህ ስመጣ ደግሞ ጀብዱ ቀርቶ የሰጡን ታርጋ ስም ተከትሎኝ መጣና በትውልድ ሃገሬ መኖር አልችል ብዬ በርሃ በቀን ስራ ቆዬሁ ይለናል፡፡
የዶክተር አብይ ወደ ስልጣን መውጣትንና የአካባቢው አመራሮች ቅን መሆናቸውን ስሰማ ወደ ሃገሬመምጣት ብፈልግም መመለሻ ገንዘብ አጣሁ፡፡ነገር ግን ከምኖርበት ቤኒሻንጉል አልመሃል ከተማ አንድ የጎጃም ልጅ ሾፌር አግኝቸ ባህር ዳር አደረሰኝ፡፡ ከባህር ዳር ደግሞ የማርቆስ ልጆች አመጡኝ ይላል፡፡ ግን ለዛሬ እንኳ የሚበላበት የለውም ፡፡ ከሰውነት ወጥቷል፡፡ ጤናውም ተቃውሷል፡፡

(ጋሻዬ ገታሁን)

Share.

About Author

Leave A Reply