ሰበር ዜና፡ በግብጽ እስር ቤት የነበሩ 32 ኢትዮጵያውያን ተለቀቁ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ በግብጽ ባደረጉት ጉብኝት ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት አብዱልፋታ አል ሲሲ ጋር ባደረጉት ውይይት በግብጽ እስር ቤት የነበሩ 32 ኢትዮጵያውያን ትናንት የተለቀቁ ሲሆን ዛሬ አዲስ አበባ ጉዞ ጀምረዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ሃላፊው አቶ ፍጹም አረጋ በትዊተር ገጻቸው እንዳሳወቁት፤ ግብጽ በሊቢያ በአሸባሪው አይ ኤስ አይ ኤስ የተገደሉ ኢትዮጵያውያንን አፅም ወደ ሀገራቸው ኢትዮጵያ ለማስመለስ በሚደረገው ጥረት ድጋፏን ለማፍድረግ ቃል ገብታለች።

 

Share.

About Author

Leave A Reply