ሰበር ዜና፤- በሌንጮ ለታ የሚመራው የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዴግ) ከኢትዮጵያ መንግስት የሚደራደር የልኡካን ቡድን ወደ ሀገር ቤት ላከ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ራሱን የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዴግ) በማለት የሚጠራውና በቀድሞ የኦነግ መስራችና መሪ በነበሩት አቶ ሌንጮ ለታ የሚመራው የፖለቲካ ፓርቲ ከመንግስት ጋር የሚደራደር ቡድን ወደ ህገር ቤት ማስገባቱን ይፋ አድርጓል።

ድርጂቱ እንደገለጸው አሁን የሚታየው አንዳንድ ለውጥ ይበልጥ እንዲጠናከርና ሰፋ ብሎ እንዲሄድ በሚል በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ መደራደር አስፈላጊ ነው ብሏል።

ውይይቱም ከግንቦት 3 እስከ 4 በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

አቶ ሌንጮ ለታ ከዚህ ቀደምም ድርጅታቸው ኦነግ በመንግስት ሽብርተኛ ተደርጎ ከተፈረጀም በኋላ አዲስ አበባ በመግባት ከኢህአዴግ ባለ ስልጣናት ጋር የተወያዩና በኋላም በአስቸኳይ ሀገር ለቀው እንዲወጡ መታዘዛቸውን መግለጻቸው አይዘነጋም። በወቅቱም በኦነግ አባልነት የተጠረጠሩ ዜጎች በወህኒ እየተጣሉ የሳቸው ከሀገር እንዲወጡ መደረጉም ለብዙዎች ጥያቄ ሆኖ አልፏል።

Share.

About Author

Leave A Reply