ሰበር ዜና፤ የኢሳት ትንታግ ጋዜጠኞች ወደ ኢትዮጵያ ሊገቡ ነው። አበበ ገላው፣ መሳይ መኮንን እና ሲሳይ አጌና ይገኙበታል

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

 

የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዢን ስቱዲዮውን በአዲስ አበባ ለማስመረቅ ከሚያደርገው ዝግጅት ጋር ተያይዞ በርካታ ጋዜጠኞቹ ወደ ሀገር ቤት ሊገቡ መሆኑ ተገልጿል።

ከእነዚህም መካከል ጋዜጠኛ አበበ ገላው፣ ሲሳይ አጌና፣ መሳይ መኮንን እና በርካታ የጣቢያው ጋዜጠኞች ወደ ኢትዮጵያ ይመለሳሉ።

ከእነዚህም መካከል የኢሳት ቦርድ ሰብሳቢ የነበረው ጋዜጠኛ አበበ ገላው እንደሚገኝበት ድርጅቱ ይፋ አድርጓል። ጉዞውን አስመልክቶ ጥያቄ የቀረበለት ጋዜጠኛ አበበ ገላው አስተያየቶቹን አቅርቧል።

በተለይም የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስትር አምባገነንነትና የኢትዮጵያውያንን ጭቆና በአለም አቀፍ መድረክ በጩሀት መግለጹን ተከትሎ ተቀናቃኞቹ ሊያደርሱበት ስለሚችሉት የጸጥታ ስጋት ተጠይቆ መልሷል።

“የእኔ ደህንነት ከሌላው ኢትዮጵያዊ አይበልጥም” ያለው ጋዜጠኛ አበበ ገላው “በወቅቱ የህዝብን ጩሀት የማሰማት ታሪካዊ ግዴታዬን ነው የተወጣሁት። ይህን ደግሞ ማንኛውም ዜጋ ሊያደርገው የሚገባ ነው” በማለት ከዚህ ጋር ተያይዞ በሚደርስበት ማስፈራርያም ሆነ የጸጥታ ችግር ሳቢያ ለኢትዮጵያዊነትና ለሰባዊነት የሚያደርገውን ትግል እንደማያቆም ገልጿል።

“ከዚህ ቀደም በሁለተኛ ምንጭ በምናገኘው መረጃ ተንተርሰን በርካታ ስራዎች ሰርተናል። አሁን ደግሞ እዝያው ህዝቡ መሀል ገብተን በራሳችን አይን እያየንና እየሰማን በሀገሪቱ ውስጥ እየተካሄደ ያለውን ተስፋ ሰጪ ለውጥ በመደገፍ የህዝቡን ጥያቄ እናስተጋባለን” ያለው የጣቢያው ቦርድ ሰብሳቢ ታማኝ በየነ “ኢሳት የየትኛውም ፖለቲካ ሀሳብ አራማጅ ሳይሆን መሰረታችን ኢትዮጵያዊነትና ሰብአዊነት ብቻ ነው” ብሏል

 

Share.

About Author

Leave A Reply