ሰበር ዜና፦ ኤርትራ የጦር ቀጣና ከሆኑ የድንበር አካባቢዎች ወታደሮቿን አስወጣች

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ኤርትራ የጦር ቀጣና ከሆኑ የድንበር አካባቢዎች ወታደሮቿን አስወጣች

በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል በተፈጸመው የሰላም ስምምነትን ተከትሎ ኤርትራ ወታደሮቿን ማውጣቷ ተዘግቧል።

ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ የመከላከያ  ሰራዊቱን ከስፍራው እንደሚያንቀሳቅስ ቃል መግባቱ ይታወሳል። ለዚህም የጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ትዕዛዝ እየተጠበቀ ነው።

በሁለቱ ሀገራት መካከል ከ20 አመት በፊት የተካሄደው ጦርነት ይህ ነው የሚባል የጎላ ጠቀሜታ በሌላት በትንሿ የድንበር ከተማ ባድመ ምክንያት ግንቦት 28 ቀን 1990 ዓ.ም ነበር የተቀሰቀሰው።

የድንበር ከተማዋ የወርቅም ሆነ የነዳጅ ዘይት ሃብት ባይኖራትም ሁለቱም ሃገራት በራሳቸው ግዛት ስር እንድትሆን ከፍተኛ ፍላጎት ነበራቸው። በወቅቱም ጦርነቱ “ሁለት መላጦች ለማበጠሪያ የሚደርጉት ፍልሚያ” በሚል ይገለፅ ነበር።

ጦርነቱ እየተስፋፋ ሲመጣ ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ ሕዝብን ለመፈናቀል ዳርጓል።

ይህ ታሪክ ተቀይሮ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ሁለቱ ሀገራት እርቅ አውርደው ህዝቦቻቸውን ዳግም ከማገናኘት አልፈው ያላቸውን የተፈጥሮ ሀብቶች በጋራ ለመጠቀም ተስማምተዋል።

 

Share.

About Author

Leave A Reply