ሰበር ዜና:- የብሮድካስት ባለስልጣን ኤልቲቪን አስጠነቀቀ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ኤልቲቪ የቴሌቪዥን ጣቢያ አስጠነቀቀ። ባለስልጣኑ የጣቢያውን ሀላፊዎች በመጥራት የቃል ማስጠንቀቅያ ሰጥቷል።

ጣቢያው ይህ ማስጠንቀቅያ የደረሰው ባለፈው ሳምንት ከአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አ.ብ.ን) ሊቀመንበር ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ በLTV Show ፕሮግራሙ ላይ ባቀረበው ቃለ መጠይቅ ሳቢያ መሆኑን ለቃሊቲ ፕሬስ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።

ብሮድካስት ባለስልጣኑ በዚህ ፕሮግራም ላይ የቀረቡት ዶ/ር ደሳለኝ ከዝግጅቱ አቅራቢ ጋር የነበራቸው ቆይታ ወደ አንድ ብሄር ያመዘነ እንደነበር በመግለጽ በጣቢያው የተላለፈውና በዩትዩብ ቻናል ላይ የተለቀቀው የቃለ መጠይቁ ቪዲዮ እንዲወርድ ጣቢያውን ከማስጠንቀቅያ ጋር ማዘዙን ነው የሰማነው።

በቃሊቲ ፕሬስ የጣቢያውን ሀላፊዎች ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት ባይሳካም የ LTV Show አዘጋጇን ጋዜጠኛ ቤተልሄም ስለ ጉዳዩ አነጋግረናታል።

ጋዜጠኛዋ እንደምትምናገረው በእርግጥም የጣቢያው ሀላፊዎች በባለስልጣኑ መስሪያ ቤት እንደተጠሩና ከውይይታቸውም በኋላ የቃለ መጠይቁ ቪዲዮ ከዩትዩብ ቻናሉ እንዲወርድ መደረጉንም ገልጻልናለች።

ጋዜጠኛ ቤተልሄም አክላም ይህ ድርጊት በጣቢያውም ሆነ በጋዜጠኞች ነጻነት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያለው መሆኑን እና በግሏም ምናልባት በተመሳሳይ ፕሮግራም ለመቀጠል የሚያስቸግራት መሆኑን ተናግራለች።

LTV Show የተሰኘው ፕሮግራም የባለ አንድ ሰው ቃለ መጠይቅ በአንጻሩ Hard Talk ተብሎ የሚጠራውን አይነት ዘውግ ያለው ሲሆን በዚህ ዝግጂት ጋዜጠኛዋ የተለያዩ የፖለቲካና የማህበረሰብ ምሁራንን በተከታታይ ስታቀርብ ቆይታለች።

 

 

Share.

About Author

Leave A Reply