ሱዳን ያሰረቻቸውን የፖለቲካ እስረኞች በሙሉ ለቀቀች

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የሱዳን ወታደራዊ ሀይል ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ ወስኗል።

ውሳኔው የተላለፈው ሀገሪቱን ለ30 ዓመታት የመሯት ኦማር ሐሰን አልበሽር ከስልጣን እንዲነሱ ከተደረገ ከሰዓታት በኋላ ነው። የፖለቲካ እስረኞች ምን ያህል እንደሆኑ ግን በዘገባው አልተገለፀም።

ወታደራዊ ሀይሉ አሁን ባወጣው መግለጫ ኢምባሲዎች እና ሚሲዮኖች መደበኛ ስራቸውን እንደሚቀጥሉም አስታውቋል። ከሀገራት ጋር የተጀመረው ግንኙነትም የሱዳንን ጥቅም ማስጠበቁ እየተረጋገጠ ይቀጥላል ነው የተባለው።

የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዳይኖሮ መስራትና ከጎረቤት ሀገራት ጋር መልካም ግንኙነትን ማሻሻልም ትኩረት እንደሚያገኙ ነው የተገለፀው።

የሱዳን መከላከያ ሀይል ሀገሪቱን ለቀጣይ ሁለት ዓመታት የሺግግር ወቅት ይመራል፡፡

Share.

About Author

Leave A Reply