ሳልቫ ኪርና ባላንጣቸው ሬክ ማቻር ሰላም አወረዱ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪርና ተቃዋሚያቸው ሬክ ማቻር የመጨረሻውን የሰላም ስምምነት ተፈራረሙ።

ሁለቱ ባላንጣዎች ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ በጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ አማካኝነት ፊት ለፊት ተገናኝተው የነበረ ቢሆንም በተካሄደው ጦርነት “ሃላፊነቱን አንተ ውሰድ አንተ” በሚል ሰጣ ገባ አለመግባባት ተፈጥሮ እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል፡

ይሁንና በቀጣዩ ቀን በኢጋድ በይነ መንግስታት አስቸኳይ ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ ሸንቆጥ የሚያደርግ ንግግር ተናግረው ነበር፡፡

በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ “እናንተ የህዝባችሁ ሰቆቃ ተሰምቷችሁ ሰላም የማታወርዱ ከሆነ ኢትዮጵያ አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ የህግም የሞራልም ግዴታ አለባት” በማለት ማስጠንቀቃቸው ይታወሳል።

ይሄው ውይይት በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱ ቀጥሎ ከቆየ በኋላ ዛሬ የሰላም ውሉን መፈራረማቸው ተሰምተቷል።

Share.

About Author

Leave A Reply