ሳዑዲ አረቢያ ኢትዮጵያውያን እስረኞችን ለመፍታት ዝግጁ መሆኗን ገለፀች

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የሳዑዲ አረቢያ መንግስት በሀገሪቱ
የሚገኙትን ኢትዮጵያዊያን እስረኞች ለመፍታት ዝግጁ መሆኑን ገለፀ።

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በሳዑዲ አረቢያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ትናንት ማምሻውን ጅዳ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በሳዑዲ ጉብኝት እያደረጉ ያሉት የሀገሪቱ ንጉስ ቢን ሳልማን አብዱልአዚዝ ባደረጉላቸው ግብዣ መሰረት መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

ጽህፈት ቤቱ አሁን ይፋ ባደረገው መረጃ የሳውዲ አረቢያ መንግስት በሀገሪቱ የሚገኙትን ኢትዮጵያዊያን እስረኞች ለመፍታት ዝግጁ መሆኑን እንደገለፀ አስታውቋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በመካከለኛው ምስራቅ በሚያደረጉት የመጀመሪያ ጉብኝታቸው ከሀገሪቱ ባለስልጠናት ጋር በሁለትዮሽና አካባቢያዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት እንደሚያደርጉም ይጠበቃል።

 

Share.

About Author

Leave A Reply