ስለ ቴፒ የሰብአዊ መብት ጥሰት ሲጮህ የቆየው ስንታየሁ ወዳጆ በሸካ ፖሊሶች ከአዲስ አበባ ታፍኖ ተወሰደ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

በቴፒ ጉዳይ ላይ በተደጋጋሚ የፍትህ ያለ እያልን ስንጮህ ከርመናል። የፌደራሉ ሆነ የክልሉ መንግስት ችግሩን ለመቅረፍ ተገቢ እርምጃ ባለመውሰዳቸው ምክንያት ባለፈው ሳምንት የብዙዎች ህይወት መጥፋቱ ይታወሳል።

የሸካ ዞን ፖሊስ መምሪያ በህግ ከተሰጠው ስልጣን እና ኃላፊነት ውጪ ዜጎችን በማፈንና በማሰር በማሰቃየት ላይ ይገኛል። አቶ የሺዋስ የተባለ የሸካ ዞን አስተዳደር ኃላፊ “ጉርማሾ” በሚል ያደራጀው ቡድን በብሔር ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እና የንብረት ውድመት በመፈፀም ላይ ናቸው።

ለምሳሌ በትላንትናው እለት ብቻ ሦስት ወጣቶች ቴፒ ውስጥ ተገድለዋል። ይባስ ብሎ ዛሬ ደግሞ በቴፒ ህዝብ ላይ የሚደርሰውን በደልና ግፍ ለመንግስትና ለህዝብ ሲያሳውቅ የነበረውን አቶ ስንታዬሁ ወዳጆን ለማሰር የሸካ ፖሊስ አዲስ አበባ ድረስ ተልኳል። በዚህ መሰረት አቶ ስንታየሁ ወዳጆ ዛሬ ጠዋት ቦሌ አከባቢ በሞተር ሳይክል በመጓዝ ላይ ሳለ የሸካ ፖሊሶች በመኪና አሳድደው ጦር መሳሪያ ከደቀኑበት በኋላ አፍነው ወዳልታወቀ ቦታ ወስደውታል።

ስለ ዜጎች መብትና ነፃነት የሚሟገቱ ሰዎች በጠራራ ፀሃይ አዲስ አበባ ውስጥ ታፍነው የሚወሰዱ ከሆነ በእውነቱ እጅግ በጣም አሳሳቢ ነው። የፌደራሉ መንግስት በአስቸኳይ ይህን የማፊያ ቡድን በቁጥጥር ስር አውሎ ተገቢ እርምጃ ሊወስድ ይገባል።

Share.

About Author

Leave A Reply