ስርዓት እና ስርዓት አልበኝነት! (ታማኝ በየነ)

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

“እግዚአብሔር ቤትን ካልሠራ ቤተ-ሠሪዎች በከንቱ ይደክማሉ::እግዚአብሔር ከተማን ካልጠበቀ ጠባቂዎች በከንቱ ይተጋሉ::”
መዝሙረ ዳዊት 126 ፥ 1

ወዳጄ እና ድንቁ አርቲስት ዶክተር ጥላሁን ገሠሠ በሸገር ኤፍኤም በቅዳሜ ከሰዓት የጨዋታ እንግዳ ፕሮግራም ላይለታዋቂዋ ጋዜጠኛ መዓዛ ብሩ እንዲህ ብሏት ነበር:- “….አሁንም እግዚአብሔር ይህቺን አገር ሊያኖራት የቻለውየጠመንጃ ብዛት አይደለም የፀሎት ብዛት ነው::…”

ከልጅነታችን ጀምሮ “ሰው በላ” እየተባልን ያደግነው የቀዳማዊኃይለሥላሴ መንግስት የኤርትራን መሬት ጨምሮ ከሶማሊያ እናከኤርትራ ተገንጣዮች የጦርነት እና የፀጥታ ስጋት እያለባትአገሪቷን በ40ሺ ሠራዊት ነበር ያስጠበቃት:: ኤርትራ ከኢትዮጵያጋር በፌዴራል ድንጋጌ በተዋቀረችባቸው የመጀመሪያዎቹዘመናት የሰሜን ዕዝ የሚባለው እና ኃላፊነቱ ለኤርትራ ጎንደር ጎጃም ትግራይ እና ወሎ ክፍለሃገራት የነበረው ክፍለጦርየሠራዊቱ ብዛት 8ሺህ ብቻ ነበር።
በአይንብሌኑ ወታደር ሳያይ ተወልዶ የሚሞት ዜጋ በዚያ ዘመን ቢኖር አያስደንቅም:: በዚያስርዓት ግን ዛሬ የምናየውን አይነት ስርዓት አልበኝነት አላየንም አልሰማንም አላነብብንም:: ለምን ይሆን?

የደርግ ስርዓት የፀጥታ መዋቅሩን ቀበሌ በሚባል አዲስ አደረጃጀት (በንጉሠ ነገሥቱ ዘመን ቀበሌ የሚባል መዋቅርአልነበረም) ወደ ህዝብ አውርዶት ነበር:: አብዮቱንምበጠባቂዎች ዲሞትፎር ሲያስጠብቀው ነበር:: የኢትዮጵያንየመከላከያ እና ፀጥታ አስጠባቂ ቁጥር እጅጉን ከፍ
አደረገው::ቁጥሩ እስከ 400ሺ ይደርስ እንደነበረ ሰምተናል:: ህዝብ ከህዝብጋር ባይገዳደልም ከአማፅያን እና ታጣቂዎች ጋር ግን የተገባው ፍጅት የዜጎችን የመኖር ዋስትና እና የመረጋጋት ተስፋ ሊሰጠውአልቻለም:: ከአብዮቱ በፊት ማጅራት መቺን እና ወሮ-በላን ይፈራየነበረው ዜጋ በአብዮት ዘመን ከመንግስት እና ታጣቂዎችየሚመጣውን ስጋት እንደተጨማሪ ዕዳ መሸከም ነው የገጠመው::

የወያኔ ስርዓት ባለፉት 27 አመታት ያየነው እና ባለፈው አንድአመት በተለይ በየቀኑ የምንታዘበው ግን በኢትዮጵያ ታሪክታይቶም ተሰምቶም አይታወቅም:: ወያኔ በሸነሸነው በአማራበትግራይ እና በኦሮሚያ ክልሎች በእያንዳንዳቸው ከሚሊዮንበላይ “ልዩ ሃይል” የሚባል ታጣቂ አለ:: የፌዴራል ፖሊስ የክልልፖሊስ የመከላከያ ሠራዊትን ስንደምረው አገሪቷ ሞልቶ የፈሰሰ”ፀጥታ አስጠባቂ” ስብስብ ያላት ይመስላል:: ነገር ግን ስርዓትአልበኝነቱ ይህንን ያህል ለምን ነገሠ? በአገራችን ሰላምና መረጋጋት ለምን ታጣ? በዘር ላይ የተመሰረተ ግጭትና ውጥረት ለምን እየተባባሰ ሔደ?

ከሰው በላው ንጉሣዊ ስርዓት ነፃ አወጣናችሁ ያሉን የመደብ እናየብሔር ፖለቲካ ልሂቃን ምን አተረፉልን? በቀስት ከመወጋት?በቁልቁል ከመሰቀል? በድንጋይ ተወግሮ ከመገደል?ከነህይወታችን ከመቃጠል? ከመፈናቀል? ከረሃብ? ከጦርነት?ከስደት? ከእስር እና ሰብዓዊ መብት መገፈፍ? … ይሄ የቁልቁለት መንገድን መቼ ነው አይናችንን ገልፀን “እኔ አልገባበትም!” ብለን ማብቂያውን የምናፋጥንለት? ይህችስ አገርጠመንጃው በዝቶ ሰላሟ መጠበቅ ካልቻለ ጥላሁን ገሠሠእንዳለውም በፀሎት እና በእግዚአብሔር ጥበቃ ከሆነ የኖርነው ልባችን ምን ያህል ቢደነድን ነው ፀሎታችንም ከሰማየ ሰማያትሊደርስልን ያልቻለው? ታዲያ ምን ተረፈን? ቂም ይዞ ፀሎት ሳልይዞ ስርቆት ሆኖብን እንዳይሆን የኢትዮጵያ ህዝብ ራሳችንንእንመርምር:: ቀስቱ ወደ ሁላችንም ቤት ሳይገባ አያርፍምና!

አገሪቷን የምትመሩት እና ለመምራት የተሰባሰባችሁ ወገኖችምየመጣችሁበት መንገድ ለህዝባችን ምንም የስርዓት እና የፍትህ ተስፋ እንዳላስገኘለት አምናችሁ በየቀኑ ወደሚታይ እናወደሚዳሰስ የመፍትሄ ጎዳና በሰከነ መንፈስ ብትፈልጉ ይበጀናል:: ከመቼውም ጊዜ በላይ የኢትዮጵያ ህዝብ በሰላም ወጥቶ እንዲገባ፤ በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች ስርዓት በቀየርን ቁጥር ስርዓት አልበኝነትን መውረሳችን መቼ ነው መፍትሄ የሚያገኘው?
በነጻነት ተዘዋውሮ እንዲሰራ የመንግስት ጥበቃን ይሻል። በዜጎች ላይ የሚደርሱ የመብት ጥሰቶች በአስቸኳይ እንዲቆሙ ይፈልጋል። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ወጣቶች ከስራ አጥነት እና የቤተሰብ ጥገኝነት ተላቀው ሰርተው የሚገቡበት ሁኔታ እንዲመቻችላቸው ይፈልጋሉ።

አንድ ህዝብ አንድ ኢትዮጵያ!

Share.

About Author

Leave A Reply