ቀይ ባህር አደርኩኝ: እንደምን ነሽ ኤርትሪያ-ደብረ ቢዘን መሳለም እሻለሁ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ቀይ ባህር አደርኩኝ፡፡ እንደምን ነሽ ኤርትሪያደብረ ቢዘን መሳለም እሻለሁ፡፡ ***** ሄኖክ ስዩም በድሬቲዩብ

ያው መጀመሪያም ሀገሬን ሁለት ቦታ አድርገዋት ነው፡፡ ከልቤ ድንበር አልነበራትም፡፡ የካህናቷ ድምጽ አለሁበት ሆኜ ይሰማኝ ነበር፡፡ ደብረ ዳሞ አናት ቆሜ ደብረ ቢዘንን በዓይኔ ለመፈለግ ቀላውጫለሁ፡፡ መረብ ዳር ወበቅ እየበላኝ ያ ማዶ ብዬ ማዶ ማዶ አይቻለሁ፡፡ እናም ኤርትሪያ ትናንትም ልቤ ላይ ድንበር አልነበራትም፤ ነገም አይኖራትም፡፡

ለኤርትራ ስለተከፈለው መስዋዕትነት ሁሌም አልጸጸትም፤ ኤርትራውያን ነጻ ሀገር ለመመስረት ዋጋ መክፈላቸውንም አልኮንንም፡፡ ይልቁንም የኢላ በረድን ብርቱካን እንደ ደብረ ገሪዛን ማጣጣም እሻለሁ፡፡ ይልቁንም እንደ ዘነበ ወላ የቀይ ባህር ሆድ አሣ ሲቀልበኝ አይቼ ትዝታውን እጽፋለሁ፡፡ ይልቁንስ የዶጋሊን የአባቶቼን ድል ስፍራው ቆሜ አጣጥማለሁ፡፡

ኤርትሪያ ጎረቤት ብቻ አይደለችም፡፡ ለዚህም ነው ፍቺ እንደመረረው ትዳር አንድ ቤት ለሁለት ከፍሎ መኖርን ምርጫ አድርገነው የኖርነው፡፡ ቀሪው ዘመናችን ሸጋ ከሆነ የባድመ ሰማዕታ በጾረና የወደቁ በቡሬ የተሰው የኤርትሪያም የኢትዮጵያም ልጆች ደም ሁሉን የሻረ ስርየት ይሆንልናል፡፡

በህልሜ ምጽዋ አደርኩ፡፡ ሸጋ አዳር ነበር፡፡ በእርግጥ ሀገርህ ላይ እንደልብ ለማደር መች ቻልክና ነው ቀይ ባህር የዘለቅኽው ትሉኝ ይሆናል፤ ሁሉም እንዲህ መልካም ይሆናል፡፡

ዳህላክ የት ነው ሳይል በዜማው የጨፈረ፤ ከጣቴ ላይ ቀለበቴ አይጠፋም ያለ፤ አምርሮ ሲጣራ ድምጹ እስከ ካሌብ ደሴት የተሰማ ኢትዮጵያዊ በጽቡቅቲዋ አስመራ ሽር ብትን ሊል ነው፡፡

እናንተ ኤርትራውያን ወንድሞቼ ከዚህ በኋላ መረብ አይበላችሁም፡፡ ድንበር አቋርጦ ሽሬ መግባት አይኖርም፡፡ የሀዋሳን ጀልባዎች እንደ ቀይ ባህር ትፈነጩባቸዋላችሁ፤ ዘጌን ገዳማት እንደ ደብረ ቢዘን ትሳለሙታላችሁ፡፡

ቅዱስ ዩሐንስን አብረን እንጨፍራለን፤ መስከረማችን የጋራችን እንደሆነው ሁሉ የጋራው ነገር የሚበዛ ልበ ሰፊ ትውልድ እንተካለን፡፡ እናም እንዲህ በሚታሰብበት ዘመን ምጽዋ ማደር አይገርምም፤ ምጽዋ ሳድር የጥይት ድምጽ አልሰማሁም፡፡

ሳዋ በምስራቅ አፍሪካ ትልቁ ዩኒቨርሲቲ ሲሆን አይቻለሁ፡፡ ክፋትና ጥላቻ ይሸነፋል፡፡ ዘመን ታሪኩን አድሶ አራት ኪሎ የፈረሰበት ጨባሽ ኮምቢሽታቶ ሲቦርቅ ያድራል፡፡ ቀይ ባህር ዳር ምጽዋ አድሮ አዲስ አበባ እንደ መንቃት ደስ የሚል ነገር የለም::

(ተሾመ ታደሰ)

Share.

About Author

Leave A Reply