ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው በሽረ እንዳስላሴ በ20 ሚሊን ብር የሚገነባ የ2ኛ ደ/ት ቤት መሰረተ ድንጋይ አስቀመጡ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው በሽረ እንዳስላሴ ከተማ በ20 ሚሊን ብር የሚገነባ የ2ኛ ደረጃት ቤት መሰረተ ድንጋይ አስቀመጡ፡፡

በዛሬው ዕለት በሽረ እንዳስላሴ ከተማ በቀዳማዊ እመቤቷ የመሰረተ ድንጋዩ የተቀመጠው የ2ኛ ደረጃ የትምህርት ቤት ግንባታ 20 ቢሊየን ብር ወጪ በኢፌደሪ ቀዳማዊ እመቤት ጽህፈት ቤት እንደሚሸፈን ታውቋል፡፡

ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው ዛሬ ረፋዱ ላይ ሽረ ከተማ ሲደርሱ የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤልን ጨምሮ የከተማው ነዋሪ ህዝብ ደማቅ አቀባበል አድርጎላቸዋል።

ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ በሽረ እንንዳስላሴ ከተማ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

FBC

Share.

About Author

Leave A Reply