ቀጣዩ የምጣኔ ሃብት ቀዉስ፡ መንግስት የሚከተለዉን ሪፖርት አድርጓል

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የአገሪቱ የብድር መጠን 27 ቢሊየን ዶለር (ወደ 1 ትሪሊየን ብር) 60 በመቶ የሀገሪቱን አመታዊ GDP
– በ 2007 የተገኘዉ ብድር 6.4 ቢሊየን፡፡በ2008 የተገኘዉ ብድር 3.4 ቢሊየን ዶላር፡፡ በ2009 ወደ 2.8 ቢሊየን ዶላር ወረደ፡፡ በ 2010 ወደ 1.1 ቢሊየን ወረደ
– በእየአመቱ የሚከፈለዉ ለብድርና ለወለድ 1.1 ቢሊየን ዶላር
– ለወደብ በአመት 1.7 ቢሊየን ዶላር
– በባለፉት 3 አመታት በአማካኝ ወደ ዉጪ ከተላከ ምርት የተገኘ ገንዝብ 3ቢሊየን ዶላር
– በአንጻሩ ከዉጪ ምርቶች ወደ አገር ቤት ለማስገባት በአመት 17 ቢሊየን ዶላር ወጪ ተደርጓል
– ወደ ዉጭ በምንልከዉ ምርትና ወደ ሃገር በምናስመጣዉ መካከል ልዩነት (trade deficit) 14 ቢሊየን ዶላር
– አሁን ያለበት የግሽበት መጠን 13.5 %
– ለሚቀጥሉት ሁለት አመታት ብቻ ብድር ለመክፈል 6 ቢሊየን ዶላር ያስፈልጋል
– ለሚቀጥሉት ሁለት አመታት ለመንግስት ፕሮጀከት ማስፈጸሚያ 7 ቢሊየን ዶላር ያስፈልጋል
– በባለፉት 15 አመታት ከኢትዮጵያ በህገወጥ የወጣዉ የገንዘብ መጠን 30 ቢሊየን ዶላር

አስቴር ማሞ እና አባይ ጸሃየ የሃገሪቱ የፖሊሲ እና ምርምር ዳይሬክተሮች አርከበ እቁባይ እና ደሚቱ የኢኮኖሚ ፖሊሲ አማካሪ አድርጋ አገሪቱ ከሾመች ሌላ ምን ይጠበቃል፡፡ እንዴት ተብሎ ነዉ የአለም ሃገራት እኮ የኢኮኖሚክ ፖሊሲያቸዉ የሚመራዉ በኖቤል ፕራይዝ ተመራጮች እና አሸናፊዎች፤ አሉ በሚባሉ የአካዳሚክስ ሰወች ነዉ፡፡ከነዚህ አገሮች ጋር መወዳደር አይቻልም፡፡

የሚቀጥሉት ሁለት አመታት ከፍተኛ ቀዉስ መፈጠሩ አይቀርም፡፡ አማራ ክልል ከጀመረዉ ቆይቷል፡፡ ሆስፒታሎች ኦክስጅን እንኳን የላቸዉም፤ እናቶች ሲዎልዱ ከጋራጅ መቶ በብየዳ እየተቀጠለ ነዉ፡፡ የሚፈለገዉ መድሃኒት የለም፡፡
ይሄን ሁሉ ጉድ ቁሞ ያየ እና የሃገሪቱን የምጣኔ ፖሊሲ እና የገንዘብ ዝዉዉር ላይ ከፍተኛ ድርሻ ያላቸዉ የብሄራዊ ባንክ ገዢ እና የንግድ ባንክ ዳይሬክተር መጠየቅ አለባቸዉ፡፡ 30 ቢሊየን ዶላር ካገር ሲወጣ አብሮ ተባባሪ ነዉ፡፡ ንግድ ባንክ ለህወሃት ሰወች በመቶ ቢሊየኖች ዶላር በኢንቨስትመንት ስም ያከፋፈል ነዉ፡፡ የኮንስትራክሽን ባንክ በህወሃት ሌቦች ከተዘረፈ በኋላ ከነ ተበላሸ ብድር ባንኩን ጠቅለሏል፡፡ነገ ደግሞ የልማት ባንክን ከነተበላሸ ብድር ብሎ ይጠቀልላዋል፡፡

ተክለወልድ አጥናፉ እና በቃሉ ዘለቀ የሚባሉ የሁለቱ ባንኮች ሃላፊዎች መባረርና መጠየቅ አለባቸዉ፡፡ ከዛም ከዩኒቨርስቲዎች የተወጣጡ ከፍተኛ የምጣኔ ሃብት ባለሙያወች ቡድን ማቋቋም አስፈላጊ ነዉ፡፡ ዋና ሌባዉን የብሄራዊ ባንክ ምክትል ገዢ እንስቶ ሌላ ቦታ ከመሾም መታሰር ነዉ የነበረበት፡፡
እሔ ሁሉ ጉድ አገር ላይ ሲሆን ብአዴን ባሀርዳር ላይ ቁጭ ብሎ 11 በመቶ እድገቱን ግለቱን ጠብቆ ለማስቀጠል እርብርብ ላይ ነን ይላል፡፡

(ሚኪ አማራ)

Share.

About Author

Leave A Reply