በሀገር ላይ ክህደት የፈፀሙ ሰዎች ለዳግማዊ_ክህደት መቀለ ላይ ተሰብስበዋል (ስዩም ተሾመ)

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

1ኛ) አቶ ስዩም መስፍን የባድመ ከተማ በ1950ዎቹ በራስ ስዩም መንገሻ ድጋፍ የተቆረቆረች መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ ሲችል ለኢትዮ-ኤርትራ ድንበር ኮሚሽን አላቀረበም!

2ኛ) አቶ ስዩም መስፍን በ1987 ዓ.ም በተካሄደው ህዝብና ቤት ቆጠራ የተመዘገቡ በባድመና አከባቢዋ የሚኖሩ የ1089 ሰዎች ስም ዝርዝርን፣ እንዲሁም በተመሣሣይ አመት በተካሄደው ብሄራዊ ምርጫ የተሳተፉ የባድመ ምርጫ ጣቢያ የመራጮችን ስም ዝርዝር ለኢትዮ-ኤርትራ ድንበር ኮሚሽን አላቀረበም!

3ኛ) ከላይ 1ኛና 2ኛ ላይ የተጠቀሱትን ተጨባጭ ማስረጃዎች ለድንበር ኮሚሽኑ ባለማቅረቡ ባድመን ለኤርትራ አሳልፎ ከሰጠ በኋላ በቴሌቪዥን ቀርቦ “ባድመና አከባቢዋ ለኢትዮጲያ ተወሰነ” ብሎ የኢትዮጲያን ህዝብ በይፋ ዋሽቷል!

4ኛ) ከተራ ቁጥር 1-3 በተዘረዘሩት ምክንያቶች በሀገር ሉዓላዊነት ላይ ክህደት ፈፅሟል!

5ኛ) አቶ ስዩም መስፍን ከላይ የተገለፀውን ጥፋትና ክህደት ሲፈፅም የህወሓት መስራቾችና አመራሮች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

6ኛ) የህወሓት መስራቾችና አመራሮች ከተራ ቁጥር 1-5 በተገለፀው መልኩ ባድመ ለኤርትራ ተላልፋ እንድትሰጥ የሚያስችለው የድንበር ኮሚሽኑ ውስኔ “ይግባኝ የሌለውና የመጨረሻ ውሳኔ ነው” የሚለውን የአልጄርስ ስምምነት ማፅደቂያ (Ratification) አዋጅ ቁጥር 225/2000 አርቅቀው በፓርላማ አፅድቀዋል፡፡

7ኛ) ከተራ ቁጥር 1-5 በተገለፀው መሠረት ባድመ ለኤርትራ ተላልፋ እንድትሰጥ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተሳታፊ የሆኑ የህወሓት መስራቾችና አመሪሮች ስለ አልጄርሱ ስምምነትና የባድመ ጉዳይ ለመወያየት ከትላንት ጀምሮ #መቀለ ላይ ተሰብሰበዋል፡፡

 

Share.

About Author

Leave A Reply