በሁመራ ከተማ የኢትዮጵያና ኤርትራ ህዝቦች የህዝብ ለህዝብ መድረክ ስነ ስርዓት እየተከናወነ ነው

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የኢትዮጵያና ኤርትራ ህዝቦች በሁመራ ከተማ የህዝብ ለህዝብ መድረክ ስነ ስርዓት በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

በዚሁ መድረክ ላይ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ደብረ ፂዮንን ጨምሮ ከሁለቱ ሀገራት የመካላከያ ኃይል አባላት፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና በሺህዎች የሚቆጠሩ የኦምሓጀርን ነዋሪዎች መገኘታቸው ነው የተገለጸው፡፡

በሁመራ ከተማ ይህ የህዝብ ለህዝብ መድረክ ስነ ስርዓት የተዘጋጀውም ታህሳስ 29 ቀን 2011 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድና ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በተገኙበት ሁለቱን ሀገራት ሚያገናኘውን የሁመራ – ኦምሓጀርን መንገድ መከፈቱን ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡

ሁለቱ ሀገራት በዚሁ አካባቢ በየብስ ትራስፖርት መገናኘት አሁን ላይ በኢትጵያና ኤርትራ ህዝቦች መካከል የተጀመረውን ሰላማዊ ግንኙነት የበለጠ እንደሚያጠናክረው ተግልጿል፡፡

FBC

Share.

About Author

Leave A Reply