በሃዋሳው ግጭት የተጠረጠሩ ታሰሩ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

በሃዋሳ ከተማ ከእግር ኳስ ጨዋታ ጋር ተያይዞ በተፈጠረ ግጭት እጃቸው አለ ያላቸውን 37 ሰዎችን ማሰሩን ፖሊስ አስታወቀ፡፡ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር 18 ሲቪሎች ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን የሞተ ሰው አለመኖሩን ፖሊስ አረጋግጧል፡፡

ከተማው ሰላማዊ እንዳይሆንና ለግል ጥቅም ሲባል ከተማዋን የሚያሸብር ቡድን አለ ያለው የከተማው ፖሊስ በምርመራ ሲረጋገጥ ይገለፃል ብሏል፡፡

ቅዳሜና እሁድ እንዲደረጉ መርሃግብር የተቆረጠላቸው ሁለት ጨዋታዎች ለከተማው ሰላምና ፀጥታ ሲባል መሰረዙን የከተማው ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ገልጿል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።

Share.

About Author

Leave A Reply