Thursday, January 17

በሐዋሳ ከተማ በዋናነት በሲዳማና_ወሊይታ ብሔር ተወላጆች መካከል የከረረ ግጭት ተፈጠረ፡፡ የበአሉ ድባብ ጠፍቷል።

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

በሐዋሳ ከተማ በዋናነት በሲዳማና_ወሊይታ ብሔር ተወላጆች መካከል የከረረ ግጭት ተፈጥሯል፡፡

የንግድ ቤቶች በግድ እንዲዘጉ እየተደረጉ ሲሆን በወላይታና የሌሎች ብሔር ተወላጆች ድብደባና ወከባ እየደረሰባቸው ይገኛል፡፡ በቦታው ወደሚገኝ ግለሰብ ጋር ስልክ ደውዬ እንዳረጋገጥኩት በተለይ አሮጌ_ገበያበሚባለው አከባቢ ነዋሪዎች መስራትም ሆነ መንቀሳቀስ የማይችሉበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡

በመሆኑም ነገሮች ከቁጥጥር ከመውጣታቸው በፊት የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት በአስቸኳይ ምላሽ ሊሰጡ ይገባል፡፡ በተያያዘ ዜና በወልቅጤ ከተማ በሚኖሩ የጉራጌ ብሔር ተወላጆችና በከተማዋ ዙሪያ ባሉት የቀቤናማህብረሰብ ተወላጆች መካከል በተፈጠረ ግጭት በአሁን ሰዓት ከወልቂጤ ወደ ወሊሶ የሚደረገው የህዝብ ትራንስፖርት ተቋርጧል፡፡

Share.

About Author

Leave A Reply