በመንግስትና በኦነግ መካከል የተደረገው ስምምነት እንዲከለስ ዳያስፖራዎች ጠየቁ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

በመንግስት እና በኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) መካከል በአስመራ የተደረገው ስምምነት እንደገና እንዲከለስ የኦሮሞ ዳያስፖራዎች ጠየቁ።

በመጣው ሃገራዊ ለውጥ ደስ ብንሰኝም በሁለቱ አካላት መካከል የተፈጠረው መቃቃር አስግቶናል ያሉት ዲያስፖራዎቹ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና ለአቶ ዳውድ ኢብሳ ግልፅ ደብዳቤ መፃፋቸውን አስታውቀዋል።

ኢቢሲ እንደዘገበው መቃቃሩ በሚሰራጭ ሃሰተኛ ፕሮፓጋንዳ መካረሩ አሳስቦናል ያሉት ዳያስፖራዎቹ፣ ሁለቱም አካላት ኃላፊነት ተሰምቷቸው ሰላም እንዲያወርዱ ጠይቀዋል።

ሁለቱም ወገኖች የወቀሳ ፕሮፓጋንዳን በማቆም ከወራት በፊት በአስመራ የደረሱበትን የስምምነት ሃሳብ እንደገና መከለስና ማጤን እንደሚገባቸውም ዳያስፖራዎቹ አሳስበዋል።

Share.

About Author

Leave A Reply