በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በመጠለያ ጣቢያ የነበሩ ተፈናቃዮች ወደቀያቸው መመለስ ጀመሩ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በመጠለያ ጣቢያ የነበሩ ተፈናቃዮች ወደቀያቸው መመለስ ጀመሩ።

ባለፉት ጊዘያት በወቅታዊ ግጭትና አለመረጋጋት ምክንያት ተፈናቅለው በአይምባ መጠለያ ጣቢያ ከነበሩት መካከል የነባሩ ጭልጋ ወረዳ ነዋሪዎች ወደቀያቸው መመለስ ጀምረዋል።

የአካባቢውን የማጋጋት ስራ ከሚያከናውኑ የዞኑ አመራሮች መካከል አቶ ደሴ ጥላሁን በተለይ ለጎንደር ፋና ኤፍ.ኤም 98 ነጥብ 1 እንደገለጹት ከላዛ እና አንከራደዛ ቀበሌዎች ተፈናቅለው የነበሩ 400 አባዎራዎችና ከ1 ሺህ በላይ ቤተሰቦች ወደቀያቸው ተመልሰዋል።

እንደ አቶ ደሴ ተፈናቃዮች ወደቀያቸው የተመለሱት የክልልና የፌደራል የጸጥታ አካላት በወሰዱት አካባቢውን የማረጋጋትና የህግ የበላይነትን የማስከባር ተግባር ሁኔታዎች በመሻሻላቸው ነው።

የእርሻ ወቅት እየደረሰ በመሆኑም ተፈናቃይ አርሶአደሮች ወደቀያቸው የመመለስና የአካባያቸውንም ሰላም የመጠበቅ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው አቶ ደሴ ተናረዋል።

በቀጣይም ከሌሎች ቀበሌዎችና ወረዳዎች ተፈናቅለው በየመጠለያ ጣቢያው የሚገኙ ተፈናቃዮችን ወደቀያቸው ለመመለስ በትክረት እየተሰራ ነው ተብሏል።

FBC

Share.

About Author

Leave A Reply