በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ባቢሌ ከተማ በህገ ወጥ መንገድ የተገኘ የጦር መሳሪያና ተጓዳኝ እቃዎች መያዙን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ዲቪዥን ኃላፊ ኮማንደር ስዩም ደገፉ ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት የጦር መሳሪያውና ተጓዳኝ እቃዎቹ የተያዙት በከተማው ትናንት ከረፋዱ አራት ሰዓት አካባቢ ህብረተሰቡ ለፖሊስ በሰጡት ጥቆማ መሰረት ነው።

የተያዙትም አራት ክላሺንኮንቭ ጠመንጃ፣ ሁለት ኤፍ ዋን የተባለ ቦንብ፣ አንድ ጸረ ታንክ ፈንጂ፣ በቁጥር 203 የክላሽ ጥይቶች፣ ሰባት የክላሽ ካርታ እንዲሁም ዲጂታል የፎቶ ካሜራ እና ሙሉ የጸጥታ አስከባሪ የደንብ ልብስ መሆኑን አስታውቀዋል።

እነዚህ የጦር መሳሪያና ተጓዳኝ እቃዎች በከተማው ከአንድ መኖሪያ ቤት ለጊዜው ወደልታወቀ ስፍራ ለማዘዋር ከሞከሩት መካከልም ሁለቱ ግለሰቦችና አንድ ተሽከርካሪ ሲያመልጡ አንድ ተጠርጣሪ መያዙን ኮማንደር ስዩም አመልክተዋል።

 

Share.

About Author

Leave A Reply