በሞያሌ ከተማ በተቀሰቀሰ ግጭት በሰው ህይወት ላይ ጉዳት መድረሱን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ሴክሬታሪያት ፅህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ሴክሬታሪያቱ እንዳስታወቀው በሞያሌ ከተማ ሚያዚያ 28፣2010 በሁለት ጎራ የታጠቁ ኃይሎች መካከል የተፈጠረው ግጭት ለሰው ህይወት መጥፋትና ጉዳት መድረስ ምክንያት ሆኗል፡፡
ቡድኖቹ በህቡዕ ሲደራጁ ቆይተው ችግሩን መፍጠራቸውን ሴክሬታሪያቱ አስታውቋል፡፡
መንግስትና የፀጥታ ኃይሎች ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን ሰላም ለማረጋገጥ እየጣረ ባለበት ወቅት በህብረተሰቡ መካከል ግጭት እንዲፈጠርና ያለመረጋጋት እንዲሰፍን በሚሰሩ ቡድኖች ምክንያት ለደረሰው የዜጎች ህይወት መጥፋት ኮማንድ ፖስቱ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ለኢቢሲ በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡
በአሁኑ ወቅት ግጭቱ በቁጥጥር ስር መዋሉን እና በድርጊቱ ላይ ተሳታፊ የነበሩትን የመለየትና የማጣራት ስራ እየተከናወነ መሆኑንም አመልክቷል፡፡
ኮማንድ ፖስቱ እንዳለው በሞያሌም ሆነ በሌሎች አካባቢዎች ለሚከሰቱ ግጭቶችና ለሚደርሰው ጉዳት ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ትልቁን ድርሻ ይይዛል፡፡
በመሆኑም በሞያሌና በተጠኑ አካባቢዎች ኮማንድ ፖስቱ ከመንግስት በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በህገ ወጥነት የተያዙ የጦር መሳሪያዎችን ማስፈታት መጀመሩንም በመግለጫው አስታውቋል፡፡

Share.

About Author

Leave A Reply