በሞያሌ ከተማ በተፈጸመ የቦንብ ጥቃት ሶስት ሲገደሉ ከ60 በላይ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ህክምና ጣቢያዎች ተወስደዋል

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

በሞያሌ ከተማ ሰላማዊ ዜጎች በሚበዙበት በከተማዋ መናሃሪያ አካባቢ በተፈጸመ የቦንብ ጥቃት እስካሁን ሶስት ሰላማዊ ዜጎች ህይወታቸው ማለፉ ተረጋግጧል። ከሟቾቹ በተጨማሪ በጥቃቱ ከመቶ በላይ ሰላማዊ ዜጎች በደረሰባቸው ጉዳት ቆስለው ወደ ከተማዋ ሆስፒታል ተወስደዋል። ጉዳት ከደረሰባቸው መሃከል ህጻናት፣ሴቶችና አዛውንቶች ይገኙበታል። የኢሳት ምንጮቻችን እንዳሉት የቁስለኞች ቁጥር ከፍተኛ በመሆኑ የሟቾች ቁጥር ሊጨምር ይችላል። በከተማዋ መናሃሪያ አካባቢ በቦረናና በገሪ ብሄረሰብ ተወላጆች መካከል ግጭት ከተከሰተ በሁዋላ ቦንብ መወርወሩን ነዋሪዎች ገልጸዋል። የከተማው መስተዳድር ኮሚኒኬሽን ሃላፊ የሶማሊ ልዩ ሃይል አባላት ጥቃቱን እንደፈጸሙት ሲገልጹ፣ የኦሮምያ ክልል ደግሞ የሶማሊ ክልል ያስታጠቃቸው ወታደሮች ጥቃቱን እንደፈጸሙት ገልጿል። የኦሮምያ ክልል በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስም የተመደቡትን ወታደሮች ተጠያቂ አድርጓል። በቅርቡ ወታደሮች ከ13 ያላነሱ ዜጎችን መግደላቸው ይታወሳል። አዲሱ ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ጅግጅጋ ባቀኑበት ወቅት የሁለቱ ክልል መሪዎች ከእንግዲህ ግጭት እንደማይነሳ ቃል ገብተው ነበር። የኦሮምያ ክልል የሶማሊ ክልል እና መከላከያን ተጠያቂ ማድረጉ ችግሩ እየሰፋ እንጅ እየቀነሰ አለመሄዱን የሚያሳይ ነው። ~ ኢሳት

Share.

About Author

Leave A Reply