በሰቆጣ የተካሄደው የድጋፍ ሰልፍ ተጠናቋል – ከተሰሙ መፎክሮች በጥቂቱ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

” ተደምረናል፤ኢትዮጵያዊነት ያኮራናል ! ” በሚል መሪ ሃሳብ በዛሬው እለት በሰቆጣ ከተማ ከጥዋቱ12 ሰዓት ጀምሮ የፍቅር እና የመደመር የድጋፍ ሰላማዊ ሰልፍ በሰላም እንደተጠናቀቀ የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር መንግስት ኮሚኒኬሽን ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ሰለሞን ተክሉ ተናግረዋል። ሰቆጣ እና መፎክሮቹ በጥቂቱ
* ይህንን የለወጥ አመራር እና የይቅርታ አመራር በፈፁም ሀገር ወዳድነት እና በትህትና እንደግፋለን።
* የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የመደመር የይቅርታ እና የለውጥ አመራርን በልብ ሙሉነት እንደግፋለን
* በዘረኝነት መቃብር ላይ አትዮጵያዊነት ለዘለዓለም በፅኑ መሰረት ይተከላል፡፡ * በቀን ጅቦች ደም ጉዞችን አይገታም።
* ፍትሃዊ የልማት ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ የበኩላችንን እንወጣለን። * “ዘርን መሰረት ያደረገ ጥቃት እናወግዛለን”
• ተደምረናል ኢትዮጵያዊነት ያምርብናል።
በግርማ ተጫነ

Share.

About Author

Leave A Reply