በሰኔ 15 የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ሕይወታቸው ያለፉ መሪዎች ሥርዓተ ቀብር ዛሬ ይፈጸማል፡፡

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 19/2011ዓ.ም (አብመድ) ባለፈው ሰኔ 15 ቀን 2011ዓ.ም በአማራ ክልል መንግሥት ላይ በተደረገው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ሕይወታቸው ያለፉ የክልሉ ከፍተኛ መሪዎች ሥርዓተ ቀብር ዛሬ በባሕር ዳር ይፈጸማል፡፡

በጥቃቱ ሕይወታቸው ያለፉት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር አምባቸው መኮንን፣ የሕዝብ አደረጃጀት አማካሪያቸው አቶ እዘዝ ዋሴ እና የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቶ ምግባሩ ከበደ የቀብር ሥነ-ስርዓት ዛሬ በባሕር ዳር ከተማ ዓባይ ማዶ ገብርኤል ይከናወናል፡፡

የቀብር ሥነ-ስርዓቱ ከመከናወኑ በፊት ደግሞ በባሕር ዳር ዓለማቀፍ ስታዲዮም የክብር አሸኛኘት ይደረግላቸዋል፡፡

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀኔራል ሰዓረ መኮንን እና ጀኔራል ገዛኢ አበራ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ደግሞ በመቀሌ የሚከናወን ይሆናል፡፡

Share.

About Author

Leave A Reply