በሰኔ 16 የቦንብ ጥቃት በተጠረተሩት ላይ ፍርድ ቤቱ የመጨረሻ ክስ ለመመስረት የ10 ቀን ጊዜ ሰጠ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

በሰኔ 16 በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ላይ በተቃጣው የቦንብ ፍንዳታ በማስተባበር፣በማዘዋወር እና በመምራት በተጠረጠሩት ባህሩ ቶላ፣ በየነ ቡላ፣ ጌቱ ግርማ እና ደሳለሽ ተስፋዬ ጨምሮ በስድስት ተጠርጣሪዎች ላይ ፍርድ ቤት የመጨረሻ ክስ ለመመስረት የ10 ቀን ጊዜ መስጠቱ ተገለፀ።

በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ተረኛ አንደኛ ወንጀል ችሎት ለዛሬ ይዞት በነበረው ቀጠሮ አቃቢ ህግ በድጋሜ ማስረጃ ይሟላ ብሎ ለመርማሪ ፓሊስ በድጋሜ መዝገቡን መመለሱን ተከትሎ መርማሪ ፓሊስም የተጠየቀውን ማስረጃ አማልቶ ለዛሬ እንዲቀርብ ፍርድ ቤቱ የተሰጠውን የጊዜ ቀጠሮ መነሻ በማድረግ ነው።

አቃቢ ህግ በባለፈው ቀጠሮ መርማሪ ፓሊስ በቦንቡ ጉዳት የደረሰባቸው ግለሰቦችን ተጨማሪ ቃልና የስልክ ልውውጥ፣ ተጨማሪ ማስረጃ እንዲያሟላ በጠየቀው መሰረት መርማሪ ፓሊስ በዛሬው ችሎት መዝገቡን አሟልቶ ለአቃቢ ህግ ማስረከቡን ገልጿል።

አቃቢ ህግ በበኩሉ የተሟላውን ማስረጃ አይቼ አጠቃላይ ክስ ለመመስረት ተጨማሪ ጊዜ ይሰጠኝ ሲል ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

ተጠርጣሪዎቹ በበኩላቸው እስከ ዛሬ ድረስ ታስረን በተደጋጋሚ ተጨማሪ ጊዜ እየተባለ ሲጠየቅ በመቆየቱ አሁንም ጊዜ ሊሰጥ አይገባም በማለት ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል።

አቃቢ ህግም ዋስትናውን በመቃወም ከወንጀል ድርጊቱ ከባድነትና ውስብስብነት አንፃር ዋስትናው ሊፈቀድ አይገባም ሲል ተቃውሟል።

የሁለቱንም ጉዳይ የተመለከተው ፍርድ ቤቱም አቃቢ ህግ በ10 ቀን ጊዜ ውስጥ ክስ እንዲመሰርት ፈቅዷል።

 

Share.

About Author

Leave A Reply