በሳዑዲ እስር ላይ የሚገኙት አላሙዲ ንብረት የሆነው ደርባ ሲሚንቶ ሥራ ካቆመ አንድ ሳምንት ሞላው

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

በሳዑዲ አረቢያ እስር ላይ በሚገኙት ሼክ መሀመድ አላሙዲና በባለቤታቸው ሳፊያ ሳላህ አላሙዲ በፈረንጆች አቆጣጠር ፌብሩዋሪ 13 ቀን 2016 ዓ.ም የተቋቋመውና በ2012 ሥራ የተጀመረው ደርባ ሲሚንስቶ ፋብሪካ ሥራ ካቆመ አንድ ሳምንት ሆነው::

8 ሺህ ቶን ሲሚንቶ በቀን ማምረት አቅም ያለው ደርባ ሲሚንቶ ሥራ ያቆመው ከአካባቢው ወጣቶች ጋር በተፈጠረ አለመግባባት መሆኑ ታውቋል::

በሙገር የሚገኘው ደርባ ሲሚንቶ ከዚህ ቀደም በተደረሰ ስምምነት የአካባቢው ወጣቶች ከድርጅቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የማከፋፈል ሥራው በአካባቢው ወጣቶች እንዲከናወን ስምምነት ላይ ተደርሶ የነበረ ሲሆን አሁን በምን ምክንያት አለመግባባት ተፈጥሮ ድርጅቱ ሥራ ለማቆም እንደተገደደ የተገለጸ ነገር የለም::

ዘ-ሐበሻ ያነጋገረቻቸው አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የድርጅቱ ሠራተና እንደገለጹት ደርባ ሲሚንቶ ሥራ ለማቆም የተገደደው ከአካባቢው ወጣቶች ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ነው ካሉን በኋላ ሌሎች ዝርዝር ጉዳዮችን አልነገሩንም::

አላሙዲ ከታሰሩ ጊዜ ጀምሮ ደርባ ሲሚንቶ ፋብሪካ በተለያዩ ጊዜያት ሥራው ሲስተጓጎል ቆይቷል:: ባለፈው ታህሳሳ ፋብሪካው በሠራተኞች አድማ የተነሳ ሥራ አቆሞ ነበር:: በወቅቱም 25 በመቶ የደመወዝ ጭማሪ ተደርጎ ሠራተኞች ወደ ሥራ ገበታቸው እንዲመለሱ መደረጉ ይታወቃል::

አሁን ደግሞ ከአካባቢው ወጣቶች ጋር በተፈጠረ አለመግባባት በአጠቃላይ ደርባ ሚድሮክ ሲሚንቶ ፋብሪካ ሥራ አቁሟል፡፡ በክምችት ያለውንም ምርት ለገበያ ማቅረብ አልተቻለም::

Share.

About Author

Leave A Reply