በሳዑዲ ዓረቢያ ታስረው የነበሩ 368 ኢትዮጵያውያን ሀገራቸው ገቡ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ኢትዮጵያውያኑ በሳዑዲ አረቢያ በተለያዩ አካባቢዎች ታስረው የነበሩ ሲሆን÷ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጅዳ ከሚገኘው ቆንስላ ጽህፈት ቤት ጋር በመተባበር ከሳዑዲ ዓረቢያ መንግስት ጋር ባደረገው ስምምነት ዜጎቹ በምህረት ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ማድረግ ተችሏል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላና ዲያስፖራ ጉዳዮች ቋሚ ተጠሪ አምባሳደር ዶክተር ቦጋለ ቶለሳ፣ የቆንሰላ ጉዳዮች ዳይሬከተር ጄነራል አቶ ዮሐንስ ሾንዴ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነብያት ጌታቸው ለዜጎቹ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የዜጎችን መብትና ክብር ከማስጠበቅ አኳያ የተጀመረውን ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያስረዳል።

መንግስት ከዚህ ቀደም ከታንዛኒያ፣ ከሱዳን፣ ከሳኡዲ አረቢያ ካስመለሳቸው በተጨማሪ ባለፈው ሳምንት 46 በሊብያ በስደት ላይ የነበሩ ኢትዮጵያውያንን መመለሱ ይታወሳል።

Share.

About Author

Leave A Reply