በቅርቡ የተቋቋመው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ሊቀመንበር ለደብረ ማርቆስ ወጣቶች ያስተላለፉት መልዕክት

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የፓርቲው ሊቀመንበር  ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ በፌስ ቡክ ገጻቸው ላይ የሚከተለውን መልዕክት አስተላልፈዋል።
ለድርጅት ስራ ባህር ዳርን ለቅቄ ወደ አንዱ የአማራ ግዛት ጉዞ እያደረግሁ ስለነበርኩ ስልኬ ባትሪ አልነበረውም:: የህዝብ ማመላለሻ ሃይገር ባስ ውስጥ ያለው ተሳፋሪም ፌስቡክ ላይ ተክሎ ሳይ የተለመደው ነገር ነው ብየ ወደ ጀመርሁት የጉዞ ንባብ ተመለስሁ:: ልክ ምሽት 2 ሰዓት ላይ ማረፊያየ ደርስሁና ስልኬን ሞልቸ ፌስቡክ ጎራ ብል ማርቆሳችን ታውካለች::

የማርቆስ ወጣቶች ሆይ:-

የአንድም ሰው ሃብትና ንብረት መቃጠል የለበትም:: እንደ በረከት ስምኦን አይነት አስገዳዮቻችን ብናገኛቸው እንክዋን ይዘን ፍትህ ፊት እንዲቀርቡ መጠየቅና አካባቢያችን ሊበጠብጡ ነው የመጡብን ብለን ለፓሊስ መስጠት እንጅ በደም ፍላትና በቁጣ አንድም ርምጃና እላፊ ነገር መፈፀም የለብንም::

እንደዚህ አይነት በሃብትና ንብረት ውድመት አንድም የኛውን የደቀቀ ኢኮኖሚ ይብሱን ይገድለዋል : ሁለቱም ደም የተጠሙ ገዳዮቻችን እኛኑ ለመምታት ሰበብ ያገኛሉ:: ስለዚህ ርምጃዎቻችና ትግላችን በጥንቃቄ : በማስተዋልና የሞራል ልዕልና ያለው ይሁን::

የሚደርሱንን መረጃዎችም በአግባቡ እንመርምር:: ከክልሉ ልዩ ሃይልም ሆነ ሌሎች ፀጽታ አካላት ጋር በመጋፈጥ የአንድም አማራ ህይወት ከዚህ በኃላ መጥፋት የለበትም:: እነ ሳሙኤል አይነት ትንታግ ወንድሞቻችንን የበሉብን ይበቃናል::

አደራ!

 

Share.

About Author

Leave A Reply