Thursday, January 17

በባህርዳር ሲካሄድ የቆየው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አመራር አባላቱን መርጦ ጉባኤውን አጠናቀቀ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

በባህርዳር ከተማ ሙሉአለም አዳራሽ በተደረገው በዚሁ ጉባኤ ንቅናቄው የአማራር አባላትን ምርጫ አካሂዷል:: በዚህም መሰረት

1-ዶር ደሳለኝ ጫኔ-ሊቀመንበር

2-በለጠ ሞላ-ምክትል ሊቀመንበርና የምርጫ ቦርድ ሀላፊ!

3-ጋሻው መርሻ-የድርጅት ጉዳይ ሀላፊ(የሰማያዊ ፓርቲ አመራር የነበረ)

4-መልካሙ ሹምየ-የፖለቲካ ጉዳይ ሀላፊ

5-አቶ ተመስገን ተሰማ-የፍትህ ዘርፍ ሀላፊ

6-አቶ ዳምጠው -የውጭ ጉዳይ ሀላፊ

7-አቶ ካሱ -የኢኮኖሚ ጉዳይ

8-አቶ ክርስቲያን ታደለ-የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ

9-ወይዘሮ መሰረት(ተመራማሪ)-ሴቶች ጉዳይ

10-አቶ የሱፍ ኢብራሄም-የህግ ጉዳዮች ተመራማሪ

11-አቶ ጥበበ ሰይፈ-የህግ ጉዳይ ሀላፊ

12-ወጣት ተሰማ ካሳሁን-የድርጅት ጉዳይና ፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ

13-አቶ ዳንኤል -የፋይናንስ ጉዳይ ሀላፊ

14-አቶ በለጠ ካሳ-የፓርቲ ፅ/ቤት ሀላፊ

ሆነዋል::

‹‹አንድ ዐማራ ለሁሉም ዐማራ፤ ሁሉም ዐማራ ለአንድ ዐማራ›› በሚል መርህ የተመሰረተው የዚህ ንቅናቄው ሊቀመንበር ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ በጉባኤው ላይ ባሰሙት ንግግር ከባለፉት 50 ዓመታት ወዲህ የአማራው ህዝብ ህልውና ወድቆ ነበር ። በ1960ዎቹ የተፈጠረው የተማሪዎች አብዮት አማራውን የበላይ አድርጎ ሌሎችን ተጨቋኝ አድርጎ አማራውን የማሳደድ እና በትጥቅ ትግሎች ጣት እንዲቀሰርበት ተደርጓል ። በዚህም አማራው ከፍተኛ መሰደድና ጭቆና እንዲሁም የፓለቲካ የበላይነት ተወስዶበታል ብለዋል።

ዐማራ ብሔር ንቅናቄም ለዘብተኛ ሊብራሊዝምን በመጠቀም የዐማራን ህዝብ ታሪክ ባህልና ትውፊት ተከብሮ በምጣኔ ሃብት ደረጃ ከሌሎች ህዝቦች ጋር እኩል ተጠቃሚ ማድረግ ነው ። በቀጣይ ፓርቲው ዲሞክራስያዊ በሆነ መንገድ ህገ መንግስታዊ ለውጦች እንዲኖሩ፤ የአማራ ህዝብ የጭቆናና የልማት ተጠቃሚነቶች እንዲረጋገጡ በክልሉና በሃገራዊ መድረኮች ተሳታፊ ይሆናል ያሉት ዶ/ር ደሳለጭ ጫንይ የአማራ ጥቅም መከበር ለኢትዮጵያ መረጋጋት ወሳኝ ነውም ብለዋል::

አማራ ጠል የሆኑ የፌዴራል እና የክልል ህጎችም እንዲከለሱ ጥሪ አቅርበዋል::

በውጭ ሃገር ያለው የአማራ ተወላጆችና ድርጅቶችም እርስ በ እርስ መሻኮቱን አቁመው በአንድነት እንዲቆሙ ጠይቀዋል::

በጉባኤው ላይ የተገኙት ጀነራል ተፈራ ማሞ በበኩላቸው በአማራው ላይ ላለፉት 27 ዓመታት የደረሰው ግፍ እንዲደራጅ ምክንያት ሆኖታል ብለዋል::

በወልቃይት የአማራ ማንነት ትግል የተነሳ ታስራ በ ቅርቡ የተፈታችው ንግስት ይርጋም እንዲሁ በባህርዳሩ ጉባኤ ላይ ተግኝታ ባሰማችው ንግግር አዲሱን የአማ ራ ብሄራዊ ንቅናቄ እንደምትደግፍና ለቆመለት አላማ አብራ እንደምትታገል ቃል ገብታለች::

Share.

About Author

Leave A Reply