በባቢሌ ወረዳ ታጣቂዎች ነፍሰጡሮችን በማመላለስ ላይ የነበረች አምቡላንስ ሾፌሩን አቁስለው አምቡላንሷን ይዘው ተሰወሩ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የሰበአዊ ዲፕሎማሲ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ

ዶ/ር ሰለሞን አሊ በጅግጅጋ ስለተፈናቀሉት ወገኖች በተመለከተ

ስታዲየም በሚገኘው ቢሯቸው ጋር ከናቲ ድሬ ጋር በመሆን አነጋግረናቸዋል፡፡

ሰበአዊነት ይቅደም! – በሚል ምላሽ ሰጥተውኛል፡፡

‹‹የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ከቤተክርስቲያን ኮሚቴዎች ጋር በመሆን በጅግጅጋ ለተፈናቀሉ 10 ሺህ ለሚገመቱ ሰዎች

1 * 3200 የታሸገ ዉሃ

2 * የመጀመሪያ የሕክምና እርዳታ መስጠት የሚያስችሉ 200 ቦርሳዎችን

የተለያዩ ንጥረ ነገር ያዘሉ ብስኩቶችን

530 የመኝታ ፍራሾችን

125 ባልዲዎችን

240 የማብሰያ እቃዎችን

400 የውሃ መያዧ ጀሪካኖች

3* 19,000 ሊትር ውሃ ያያዘ የውሃ ቦቴ ከአዲስ አበባ ተነስቷል – ማለዳ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል

4* 47000 ኪሎ ግራም ሩዝ እንዲሁም 400 የተለያዩ ንጥረ ነገር ያየዙ ብስኩቶችን ከአዲስ አበባ እንዲሁም ከሐረር ልከናል

በመጨረሻም ማሳሰቢያ ነግረውናል!

የባቢሌ ወረዳ አምቡላንስ ኢት ኮድ 5 የሠሌዳ ቁጥር 01966

ነፍሰጡሮችን በማመላለስ ላይ የነበረች አምቡላንስ

ያልታወቁ ታጣቂዎች ሾፌሩን አቁስለው አምቡላንሷን ወስደዋታል፡፡

ሾፌሩ በሐረር ፋና ሆስፒታል በሕክምና ላይ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የሰበአዊ ዲፕሎማሲ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ

ዶ/ር ሰለሞን አሊ አፋልጉኝ ሲሉ ለሀገር መከላከያ ደብዳቤ መጻፋቸውን አስረድተውናል

Share.

About Author

Leave A Reply