በቤኒሻንጉልና አሶሳ ተፈጥሮ በነበረው ግጭት እጃቸው አለበት የተባሉ ባለስልጣናት ፍርድ ቤት ቀረቡ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳና ሸርቆሌ ወረዳዎች ከሰኔ 16 ጀምሮ ተከስቶ በነበረው የፀጥታ ችግር የተጠረጠሩ 46 የክልሉ ፀጥታ መዋቅር አባላትና ግለሰቦች በትላንትናው ዕለት በአሶሳ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀረቡ።

ፍርድ ቤቱ ነዋሪዎችን በብሔር በመከፋፈልና ወጣቶችን በማደራጀት በሰው መግደልና የመገድል ሙከራ፣ በአካልና በንብረት በደረሰ ጉዳት በተጠረጠሩት በነኮማንደር ኡስማን አህመድ የክስ መዝገብ የቀረቡ የአምስት ግለሰቦችን ጉዳይ ተመልክቷል፡፡

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን መርማሪ ቡድንም የምርመራ መዝገቡን በሰውና በሰነድ ማስረጃ ለማደራጀት የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ጠይቆ ፍርድ ቤቱ በ10 ቀናት ውስጥ ተጠናቆ ለሐምሌ 12 እንዲቀርብ አዟል።

በአሶሳ ዞን ሸርቆሌ ወረዳ ሰኔ 20 በተፈጠረው የፀጥታ ችግር በመሳተፍ በሰው ህይወት፣ አካልና ንብረት ላይ በደረሰው ጉዳት የተጠረጠሩ 41 ግለሰቦችም በአሶሳ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንደቀረቡም ተገልጿል፡፡

መርማሪ ቡድኑ የምርመራ መዝገቡን በሰውና በሰነድ ማስረጃ አስደግፎ ለማቅረብ የጠየቀው የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮም ተቀባይነት በማግኘቱ ለሐምሌ 18 ተቀጥሯል፡፡

 

ምንጭ፦ኢዜአ

 

Share.

About Author

Leave A Reply