በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የታጠቁ ኃይሎች የሰዎች ህይወት ማጥፋታቸው ተገለፀ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ ዳጉ ኮከል ቀበሌ ማንነታቸው ያልታወቀ የታጠቁ ኃይሎች ባደረሱት ጥቃት የሰዎች ህይወት ማለፉን የክልሉ መንግስት ገለጸ።

ህይወታቸው ካለፈው ሰዎች መካከል አብዛኞቹ ሴቶችና ህጻናት መሆናቸው ነው የተገለጸው፡፡

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሰላም ግንባታና ደህንነት ቢሮ ኃላፊ አቶ አበራ ባየታ በጥቃቱ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎችም በፓዊ ሆስፒታል በህክምና ላይ እንደሚገኙ ገልፀዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት የሀገር መከላከያ ሰራዊትና የክልሉ ልዩ ኃይል ሁኔታዎችን እየተከታተሉ ሲሆን፥ ሁኔታዎች ወደ መረጋጋት እየመጡ መሆናቸው ተመልክቷል።

Share.

About Author

Leave A Reply