በብርጋዴር ጄኔራል ሀይሉ ጎንፋና አባ ነጋ ጃራ የሚመራው የተባበረው ኦሮሞ ነፃነት ግንባር አባላት አዲስ አበባ ገቡ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

በብርጋዴር ጄኔራል ሀይሉ ጎንፋና አባ ነጋ ጃራ የሚመራው የተባበረው ኦሮሞ ነፃነት ግንባር አባላት የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው አዲስ አበባ መግባታቸው ተገለፀ።

የግንባሩ አባለት በዛሬው ዕለት ሲገባ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ካሳሁን ጎንፌ በቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የተባበረው ኦሮሞ ነፃነት ግንባር የመንግስትን ያቀረበውን ጥሪ በመቀበል የትጥቅ ትግሉን በማቆም ከመንግስት ጋር ለመነጋገርና በሰላማዊ የፖለቲካ ሜዳ ለመሳተፍ መግባቱን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አስታውቋል።

የግንባሩ የግንባሩ ምክትል ሊቀመንበርና ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ብርጋዴር ጄኔራል ሀይሉ ጎንፋ በበኩላቸው መንግስት ያቀረበውን ሰላማዊ ጥሪ ተከትሎ የትጥቅ ትግሉን በማቆም ሰላማዊ ትግል ለማድረግ ወደ ሀገር መግባታቸውን አስታውቀዋል፡፡

ግንባሩ ከህዝብ ጋር በመሆን እንደሚሰራ ያስታወቀ ሲሆን፥ ባለፉት ሶስት ወራት በሀገሪቱ እየታዩ የሚገኙ ለውጦችን እንደሚደግፉ እና ለውጡ ቀጣይነት እንዲኖረው ከመንግስት ጎን እንደሚቆም ፡፡

ግንባሩ ከህዝብ፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎችና ከመንግስት ጋር በመሆን ለመስራት እቅድ መያዙን ነው ያስታወቀው።

 

Share.

About Author

Leave A Reply