በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአደጋ ጊዜ ፈንድ በኢትዮጵያ ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች 15 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አደረገ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአደጋ ጊዜ ፈንድ በኢትዮጵያ ከቀያቸው ለተመዛበሉ ዜጎች ህይወት ለማዳን የሚውል 15 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ለቋል፡፡ የድርጅቱ ማእከላዊ የአደጋ ጊዜ ምላሽ ሰጪ ፈንድ በኢትዮጵያ በግጭት ምክንያት ከመኖሪያቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ የሚውል አስቸካይ የገንዘብ እርዳታ ዛሬ ለቋል፡፡

በአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ አመራርነት በሀገሪቱ አዲስ የአንድነትና የመደመር እርምጃዎች እየመጣ መሆኑ የገለጹት የድርጅቱ ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ይሁን እንጂ በሀገሪቱ አንድ አንድ አከባቢዎች በሚከሰቱ ግጭቶች ምክንያት የሚፈናቀሉ ዜጎች ለአመራሩ ችግር ሊሆኑት እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡

ለችግሩ አስቸካይ መፍትሄ ለመስጠት ድርጅቱ 15 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ መልቀቁም ዋና ጸኃፊው ተናግረዋል፡፡ መንግስት በሚያደርገው የህይወት አድን እርዳታ የድርጅቱ ሰብአዊ እርዳታ ፋይዳው የላቀ ሲሆን ድጋፉ ከ36 ሺ በላይ ዜጎች አስቸካይ የአልሚ ምግብ፣ 600 ሺ የውኃ፣ 71 ሺ 200 ዜጎች ከምግብ ውጪ ቁሳቀስ እንዲሁም 175 ሺ ዜጎች የጤና ኬላ አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችል ነው፡፡

ምንጭ፡- Africa-newsroom

 

Share.

About Author

Leave A Reply