በተጠርጣሪ ብርሃኑ ጃፈር ላይ አቃቤ ህግ እስከ መስከረም 16 ቀን ክሱን እንዲመሰርት ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጠ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

በሰኔ 16 የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የድጋፍ ሰልፍ ላይ በራሱ መኪና በመጫን ተጠርጣሪዎችን ቦምቡ የፈነዳበት ቦታ ድረስ በመሸኘት የተጠረጠረው ብርሃኑ ጃፋር ላይ ጠቅላይ አቃቢ ህግ እስከ መስከረም 16 ቀን ክሱን እንዲመሰርት ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጠ፡፡

በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ተረኛ አንደኛ የወንጀል ችሎት ለዛሬ ይዞት የነበረው ቀጠሮ አቃቢ ህግ ክስ ለመመስረት ጊዜ ይሰጠኝ ብሎ የተሰጠው የዘጠኝ ቀን ክስ የመመስረቻ ጊዜ መሰረት ክሱን ለመመልከት ቢሆንም አቃቢ ህግ በዛሬው ዕለት ክሱ እንዳልደረሰለት አብራርቷል፡፡

አቃቢ ህግ የወንጀል ህጉን ለይተን እያዘጋጀን ያለን ቢሆንም የተጎጂዎችን ጉዳት መጠን ሆስፒታል በመገኘት ለማረጋገጥ ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ስራችን ላይ ተጽዕኖ ስለፈጠረ በተባለው ቀነ ለማቅረብ አልቻልንም ሲል ክስ ያለመመስረቱ ምክንያት አቅርቧል፡፡

በዚህም አቃቢ ህግ ክሱን አጠናቆ ለማቅረብ 10 ቀን ይሰጠኝ ሲል ፍርድ ቤቱን ጠይቋል፡፡

የተጠርጣሪ ጠበቃ በበኩሉ አቃቢ ህግ ያቀረበውን ምክንያት ተገቢነት የሌለው የተጠርጣሪውን መብት የሚጎዳና የፍርድ ቤቱን ጊዜ የሚሻማ መሆኑንም ከግምት ውስጥ ገብቶ ተጠርጣሪው በዋስ እንዲወጡ ጥያቄ አቅርቧል፡፡

ግራ ቀኙን ያደመጠው ፍርድ ቤትም የተጠርጣሪውን የዋስትና ጥያቄ በማለፍ አቃቢ ህግ እስከመስከረም 16 ቀን ክሱን አጠናቆ እንዲቀርብ ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡

በታሪክ አዱኛ

Share.

About Author

Leave A Reply