በትግራይ ልዩ ቦታው ኩያ በስውር ማጎሪያ ቤት የታሰሩ የመከላከያ አባላት የድረሱልኝ ጥሪ እያስተጋቡ ነው::

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

በትግራይ ክልል ከፌደራሉ መንግስት እውቅና ውጭ በሚገኝ ስውር ማጎሪያ ቤት ታሰረው የሚገኙ የመከላከያ አባላት የምህረት አዋጁ ተጠቃሚ እንዳይሆኑ ከመከልከላቸው በተጨማሪ ኢ-ሰበአዊ ድርጊት እየተፈጸመባቸው በመሆኑ የድረሱልኝ ጥሪ አስተላልፈዋል::

የሰሜን እዝ የመከላከያ አባላን በብሄራቸውና በማንነታቸው በድብቅ የሚያሰቃይበት የኩያ ስውር እስር ቤት ከፌደራሉ መንግስት እውቅና ውጭ በመሆኑ በመንግስት ለመከላከያ አባላት የተሰጠውን የምህረት አዋጅ መጠቀም ሳይችሉ እስካሁን ድረስ ኢ-ሰበአዊ ድርጊቶች እየተፈጸሙባቸው መሆኑን መረጃዎች ደርሰውናል።

በዚህ ስውር ማጎሪያ ቤት ባሉ የመከላከያ አባላት ላይ በጨለማ ቤት ከመወርወር ጀምሮ አካላዊ ጥቃቶች ጭምር እየተፈጸመባቸው እንደሆነ ለማረጋገጥ ተችሏል። ከቦታው የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው ቦታው ከመንግስት እውቅና ውጭ በመሆኑ መንግስት ይህንን ስውር ማጎሪያ ቤት በመፈተሽ በመከላከያ አባላቶች ላይ አካላዊና ኢ-ብአዊ ድርጊቶችን እየፈጸሙ ያሉ አካላት በህግ እንድጠየቁና የታሰሩ የመከላከያ አባላት እንድፈቱ መረጃው ጠቅላይ ሜኒስተር ጽ/ቤት,መከላከያ ሜኒስተር እና ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት እንድደርስላቸው እየጠየቁ ነው።

የ 92 ግዞተኞች ስም ዝርዝር ከታች በፎቶው ተያይዟል::

(ልሳነ-አማራ)

Share.

About Author

Leave A Reply