በትግራይ ክልል በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ14 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ሁለት ህፃናት ጉዳት ሳይደርስባቸው ተረፉ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

በትግራይ ክልል በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ14 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ሁለት ህፃናት ጉዳት ሳይደርስባቸው ተረፉ:: በትግራይ ክልል ምስራቃዊ ዞን ጋንታ አፈሹም ወረዳ፣ አዘባ ጣቢያ በተባለ አካባቢ በትናትናው ዕለት በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ14 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

በዚህ የትራፊክ አደጋ በ15 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰ ሲሆን፥ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎችም በአዲግራት ሆስፒታል የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛሉ፡፡

በዚህ አደጋ ሁለት ህፃናት ምንም አይነት ጉዳት ሳይደርስባቸው እንደተረፉ ተገልጿል፡፡ ህፃናቱ በአሁን ወቅት በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ተነግሯል፡፡

አደጋው ያጋጠመው የህዝብ ማመላሻ አውቶብስ 31 ሰዎችን አሳፍሮ ከአዲግራት ከተማ ወደ አዘባ ጣቢያ በሚጓዝበት ወቅት ፎጋ ቂዓት በሚባል ቦታ ገደል ውስጥ በመግባቱ ምክንያት መሆኑን የወረዳው የትራፊክ ፓሊስ አስተባባሪ ዋና ሳጅን ርግበ ገብረትንሳኤ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አስታውቀዋል፡፡ የአደጋው ምክንያት በመጣራት ላይ እንደሚገኝም የትራፊክ ፓሊስ አስተባባሪው ተናግረዋል፡፡

Share.

About Author

Leave A Reply