በችኮላ የሚካሄድ የሕዝብ ቆጠራ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የሕዝብ ቆጠራ እንደሚደረግ እየሰማን ነው። CSA (central statistical Agency) ወይም የሕዝብ ቆጠራ መስሪያ ቤት ገለልተኛ መስሪያ ቤት አይደለም። የሕዝብ ቆጠራው ውጤት የፖለቲካ ፍልጎት እንዲያንጸባርቅ ሲያደረግ የነበር መስሪያ ቤት ነው። ያ ብቻ አይደለም በቆጠራው የሚጠየቁ ጥያቄዎች ሳይቀሩ ለሕዝቡ ትክክለኛ ምርጫ የሚያቀረቡ አይደለም።

ለምሳሌ :- የአፍ መፍጫ ቋንቋ ይጠይቃሉ፤ ግን ተደራቢ ቋንቋ አይጠይቁም። ወይም ጠይቀዉም ከሆነ ይፋ አያደረጉም።ለምን ብትሉ እንደ አፍ መፍቻና ተደራቢ ቋንቋ አማርኛ የሚናገረው ማሀብረሰብ ወደ ሰባ ሰማኒያ በመቶ የኢትዮጵያ ህዝብ ሊሆን እንደሚችል ማሳወቅ ስለማይፈለጉ ነው። አዲስ አበብን ብትወስዱ ወደ ዘጠና ስምንት በመቶ ነዋሪዎው አማርኛ ተናጋሪ ነው፤ እንደ አፍ መፍቻ ወይንም ተደራቢ ቋንቋ።

ብሄር ብሀረሰብ የሚኡትን ይጠይቃሉ፣ ግን ከተለያዩ ብሄረሰቦች የሆኑ ከአንድ በላይ ብሄረሰብ እንዲጠቅሱ አይፈቀድላቸውም። እናቱ አማራ፣ አባቱ ኦሮሞ የሆነ ፣ አንዱን መምረጥ ይገደዳል። ያ ብቻ አይደለም አንድ ሰው ኦሮሞ፣ ወይንም ትግሬ፣ ወይንም ጉራጌገ ስለመሆኑ ትክክለኛና ሳይንሳዊ መመዘኛ የለም።

በአጠቅላይ የሕዝብ ቆጠራው ተቀባይነትና ተዓማኒነት እንዲኖረው ከተፈለገ በገለልተኛ ተቋም መከናወን አለባት። የሚቀርቡ ጥያቄዎችም በግልጽ ይፋ ሆነው ሕዝብ አስተያየት እንዲሰጥባቸው መደረግ አለበት። በተለይም ብሄር ብሄረሰብህ ምንድን ነው የሚለው ጥያቄ አስፈላጊነት ላይ መወያየት ያስፈልጋል። በኔ እይታ ብሄር ብሄረሰባ የሚለው ጥያቄ መጠየቅ የለበትም ባይ ነኝ። አስፈላጊም አይደለም። ዜጎች የሚናገሩት ቋንቋ ከታወቀ ያ በቂ ነው። በዚያ መሰረት ዜጎች በቂዉን መንግስታዊ አገልግሎት እንዲያገኙ ማመቻቸት ይቻላል።

(ግርማ ካሳ)

Share.

About Author

Leave A Reply