በኒውዚላንድ መስጊዶች ላይ በተከፈተ ተኩስ በርካቶች ተጎዱ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ዛሬ በኒውዚላንድ ክሪስትቸርች ከተማ ሁለት መስኪዶች ላይ በተከፈተ ተኩስ ብዙዎች መጎዳታቸውን ፖሊስ አስታወቀ።

በጥቃቱ እጃቸው አለበት ተብሎ የተጠረጠሩ ሶስት ወንዶችና አንዲት ሴት በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ፖሊስ ጨምሮ ገልጿል።

የኒውዚላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ጃሲንዳ አርደርን ጥቃቱ የተፈፀመበት ይህ ቀን የአገሪቱ ጨለማ ቀን ነው ብለዋል።

የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን ደግሞ በቁጥጥር ስር ከዋሉት አንዳቸው አውስትራሊያዊ መሆናቸውን አስታውቀዋል።
ተጠርጣሪዎቹንም “ፅንፈኞች፣ ቀኝ ዘመም አሸባሪዎች” ብለዋቸዋል።

ሁኔታው እስካሁን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ባለመዋሉ ፖሊስ በጥቃቱ ምን ያህል ሰዎች ስለመሞታቸው ያለው ነገር የለም።

 

Share.

About Author

Leave A Reply