በአለም ቅርስነት የተመዘገበው የሲዳማ ብሄር የዘመን መለወጫ ፊቼ ጨምበላላ በዓል ከዛሬ ጀምሮ በተለያዩ ስነ ስርዓቶች መከበር ጀምሯል።

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

በሀዋሳ ከተማ መከበር የጀመረው የሲዳማ ብሄር የዘመን መለወጫ ፊቼ ጨምበላላ በዓል እስከ ነገ ድረስ በተለያዩ ስን ስርዓቶች ደምቆ እንደሚቆይ ተነግሯል።

በበሲዳማ ዞን ከሚገኙ ወረዳዎች የተውጣጡ የሃገር ሽማግሌዎች በበዓሉ ላይ “የቄጣላ” ጨዋታና የፈረስ ጉግስን ጨምሮ የተለያዩ ዝግጅቶችን የሚያከናውኑ ይሆናል።

በዓሉ በዞኑ ወረዳዎች ለተከታታይ ሁለት ሳምንታት በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚከበርም ታውቋል፡፡

የደቡብ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፀው፥ በዓሉን ለማክበር አስፈላጊውን ዝግጅት ሲያከናውን ቆይቷል።

የቢሮው ምክትል ሀላፊ አቶ ለማ መሰለ፥ ፊቼ ጨምበላላ በዓልን ምክንያት በማድረግ ወደ ከተማዋ ለሚመጡ ጎብኚዎች የክልሉን ባህል ለማስተዋወቅ እንደሚንቀሳቀሱም ተናግረዋል።

የሲዳማ ብሄር ዘመን መለወጫ ”ፊቼ ጨምባላላ” በዓል በተባበሩት መንግስታት የሳይንስ፣ የትምህርትና የባህል ማእከል (ዩኔስኮ) በማይዳሰስ ቅርስነት የተመዘገበው በ2008 ዓ.ም ህዳር ወር ላይ መሆኑ ይታወሳል።

 

Share.

About Author

Leave A Reply