በአልበሽር ላይ ከህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር ጋር በተያያዘ ምርመራ ተጀመረ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የሱዳን አቃቤ ህግ በሃገሪቱ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ኦማር ሃሰን አልበሽር ላይ ከህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር ጋር በተያያዘ ምርመራ ማካሄድ ጀመረ። የሃገሪቱ መንግስት አቃቤ ህግ በበሽር መኖሪያ ቤት በርካታ መጠን ያለው ገንዘብ መገኘቱን ተከትሎ ነው ማጣራቱን የጀመሩት ተብሏል።

በቤታቸው በተደረገው ፍተሻ ከ351 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላር እና 6 ሚሊየን ዩሮ የያዙ ሻንጣዎች ተገኝተዋል ነው የተባለው። ከዚህ ባለፈም 5 ሚሊየን የሱዳን ፓውንድም በሻንጣ ተገኝቷል።

ሬውተርስ ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው አቃቤ ህግ በህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር፣ ከፍተኛ መጠን ያለው የሃገር ውስጥና የውጭ ሃገራት ገንዘቦችን አላግባብ በመያዝና በማከማቸት ፕሬዚዳንቱ ላይ ምርመራ ጀምሯል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም የቀድሞውን ፕሬዚዳንት ፍርድ ቤት ቀርበው በጉዳዩ ላይ ማብራሪያና ምላሽ እንዲሰጡም ማዘዙንም ዘገባው ያመላክታል። ከዚያ ቀደም ብሎ ግን ከፍተኛ ጥበቃ ወደ ሚደረግበት ኮባር ማረሚያ ቤት በማምራት ከጉዳዩ ጋር የተያያዘ ጥያቄ እንደሚጠየቁም ምንጮች ገልጸዋል።

በአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በምዕራብ ዳርፉር ከተፈጸመው ጭፍጨፋ ጋር በተያያዘ የእስር ትዕዛዝ የተቆረጠባቸው አል በሽር፥ ከ9 ቀናት በፊት በሃገሪቱ ጦር ከስልጣን ተወግደው ማረሚያ ቤት ይገኛሉ።

ምንጭ፦ አልጀዚራ

Share.

About Author

Leave A Reply