Thursday, January 17

በአማራ ክልል በእቅድ ብቻ የቀሩ 35 የመንገድ ፕሮጀክቶች

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +
 1. ከሀሙሲት-እስቴ- ሁለት ግዜ የዉጭ እርዳታ ተገኝቶለት ያልተሰራ ገንዘቡም የት እንደገባ ያልታወቀ በሚዲያ በተደጋጋሚ ተነግሮለት የቀረ
 2. ከደብረማርቆስ-በረቡዕ ገቢያ-ሞጣ፡ በተደጋጋሚ ቃል እየተገባና እየተለካ የቀር
 3. ከዳንግላ-ጃዊ፡ ቃል ተገብቶ የቀረ
 4. በኩታበር-ወገልጠና-በጌምድር ከዛሬ 20 አመት ጀምሮ ቃል ለህብረተሰቡ በየ 5 አመቱ እየተገባ የቀረ
 5. ከሞጣ-እስቴ-ደብረታቦር-እብናት፤ ከሶሰት አመት በፊት ተጀምሮ የቀረ
 6. ከደብረታቦር-ሐሙሲት-ስማዳ (በጉና ተራራ ምዕራባዊ በኩል) በ2002 ምርጫ ሥራ ተጀምሮ ምርጫዉ እንዳለቀ ሥራዉ የቆመ
 7. ከጋሸና-ላሊበላ ከሃያ ዓመት በኋላ የተጀመረ አሁን እጅግ ጥራቱ በወረደ መልኩ እየተሰራ ያለ
 8. ከቡሬ-ወለጋ ደረጃዉን የጠበቀ አስፓልት ከሶሰት አመት በፊት ይሰራል ተብሎ የነበረ
 9. ከኮምቦልቻ-ምስራቅ ጎጃም በተሰራ በ 3 ወሩ ፈራርሶ አሁን ለአገልግሎት የማይሆን
 10. ከመርሐ ቤቴ-አዲስ አበባ ደርጃዉን የጠበቀ መንገድ ይሰራል ተብሎ የቀረ አሁን አፈር እየደለደሉ የተዉት
 11. ከዳባት-ጸገዴ-ወልቃይት ይሰራል በሚል ከገበሬዉ ሙጭጭ ብለዉ በሬና ፍየሉን ከወሰዱ በኋላ የተሰወሩ፡፡ ዘንድሮ በግርግሩ ምክንያት ለሁለተኛ ጊዜ በጥቀምት ወር የመሠረት ድንጋይ አስቀምጠዋል
 12. ከጎንደር-ቆላድባና ከጎንደር ጎርጎራ ደረጃዉን የጠበቀ አስፓልት ከ 15 አመት በፊት ታቅዶ ያልተሰራ (ወደ ጎርጎራ ያለዉ ተበጣጥሶ ሽሮ ፈሰስ ስሪት ሰርተዉት መፍረስ ጀምሯል)
 13. ከጢቅ-ፈለገብርሃን በ 3 ዓመት መጠናቀቅ ሲገባዉ ከተጀመረ 9 አመት የሆነዉ
 14. ከደጀን-ጀማ ወንዝ መጠናቀቅ የነበረበት ከ 7 አመት በፊት ሲሆን እስካሁን በመንቀራፈፍ ላይ ይገኛል
 15. ከመቅደላ ወረዳ-ደቡብ ጎንደር-ጋይንት የሚያገናኝ መንገድ በሚሊኒየሙ በደመቀ መኮነን የመሰረት ድንጋይ ተጥሎለት ያልተጀመረ ወይም የቀረ
 16. ደሴ-ሮቢት ገብያ መስመር-ደሴ ከመናፈሻ-ከደሴ-አቃስታ፡፡ ሁሉም ከዛሬ 7 አመት በፊት ተቆፍሮ ሳይሰራ የቀር
 17. ጣርማ በር-ሞላሌ-መሐል ሜዳ- ሊሰራ ገንዘብ ተመድቦለት ከ 3 ጊዜ በላይ የተሰረዘ
 18. ከባህር ዳር -ጢስ አባይ አስፓልት መንገድ የመሰረት ድንጋይ ተጥሎለት በጀት ተይዞለት ያልተሰራ
 19. ከደብረብርሃን-አዋሽ አና ከደብረብርሃን-አንኮበር አስፓልት መንገድ በጀት ተይዞለት የቀረ

 

 1. ባህር ዳር ላይ አዲስ የአባይ ድልድይ ከአሮጌዉ ድልድይ በስተደቡብ በኩል በጠቅላይ ሚኒሰትሩ ቃል ተገበቶ መና ሁኖ የቀረዉ

 

 1. ከእብናት-አምደወርቅ ደረጃዉን የጠበቀ የጠጠር መንገድ ቃል ተገብቶና ተጀምሮ የቀረ

 

 1. ከአዲስ አበባ-ላሊበላ-ወልደያ-ደላንታ-ተንታ-አቃስታ-ቦረና-ወራሂመኑ-ጃማ-ዓለም ከተማ ፕሮጀክት ተቆራርጦ በየቦታዉ ተጅምሮ የቀረ

 

 1. ከጭልጋ-አይከል-ማሰሮ ደንብ-መሀል አርማጭሆ-አሸሬ-ሁመራ፡፡ በ1992 ጥናቱ አልቆ ለህዝብ በ 3 ዓመት እንሰራዋለን ብለዉ የመሰረት ድንጋይ ጥለዉ፤ አሁን ከብጥብጡ ወዲህ ለሁለተኛ ጊዜ የመሰረት ድንጋይ ተጥሉዋል
 2. ከደሴ-ሳይንት-ስማዳ-እስቴ-ባህርዳር ምርጫ በመጣ ቁጥር ለአካባቢዉ ሀዝብ ቃል እየተገባለት ያልተሰራ
 3. ወራኢሉ-ጉጅፍቱ-አለም ከተማ፡ ሁለት ግዜ የአስፓልት መንገድ ሊሰራ ተጀምሮ የቀረ
 4. የኮምቦልቻ-መካነሰላም-ግንደወይን አስፓልት የታጠፈ
 5. ከወገራ-በለሳ-ዋግምራ ቤት ሁሉ ተቀብቶ የቀረዉ መንገድ
 6. ከአዲስ ዘመን-በለሳ-ሐሙሲት
 7. ከደብረብርሃን-እነዋሪ አስፓልት ሊሰራ ተብሎ በጀት ተይዞለት የጠፋ
 8. ከባህርዳር-ድልሸት-ጨንታ፤ የአስፓልት መንገድ በጀት ተመድቦለት የቀረ
 9. ከላይ ጋይንት-ታች ጋይነት-አ.አ፤ደረጃዉን የጠበቀ መንገድ ይሰራል ተብሎ በየምራጫዉ ጊዜ ቃል የተገባ
 10. ከደንበጫ-ፈረስ ቤት-ደጋዳሞት
 11. ከባህርዳር-አዴት-ፈረስቤት-ደብረማርቆስ የመሰርት ድንጋይ ተጥሎለት የቀረ
 12. ከመተማ-አብርሃ ጅራ (ዘንድሮ ለሶስተኛ ጊዜ የመሰረት ድንጋይ ተጥሎለት ለሆነ ለትግሬ ካምፓኒ ተሰቷል)
 13. ከአዘዞ-ጎንደር (ይሄን መንገድ ጣሊያን እንደሰራዉ ነዉ በየጊዜዉ ብቻ አፈር ይሞሉታል)፡

ምንጭ:_ ልሳነ አማራ

Share.

About Author

Leave A Reply