በአማራ ክልል ደምበጫ ወረዳ ከካናቢስ ለሚዘጋጅ መድሃኒት የፋብሪካ ግንባታ ፍቃድ እንዳልሰጠ መንግስት አስታወቀ።

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

በአማራ ክልል ደምበጫ ወረዳ ከካናቢስ ለሚዘጋጅ መድሃኒት የፋብሪካ ግንባታ ፍቃድ እንዳልሰጠ መንግስት አስታወቀ።

የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶክተር አሚር አማን የካናቢስ ምርትን በሀገሪቱ ለመድኀኒትነትም ሆነ ለሀገር ውስጥና ለወጪ ንግድ ማምረት የጤና ሚኒስቴር ፍቃድም ሆነ እውቅና አልሰጠም ብለዋል።

ሚኒስትሩ በተለያየ ጊዜ ከተለያዩ ሀገራት ለሚመጡ ባለሀብቶችም የካናቢስ ምርት የሚከለከል መሆኑን በተደጋጋሚ ማሳወቃቸውን ነው ያስታወቁት።

የአማራ ክልል መንግስትም ባወጣው መግለጫ አንድ አንድ አካላት በሀገርና በዜጎች ጤንነት ላይ አደጋ ከሚያደርሰው የካናቢስ ዕፅ መድሃኒቶች ለማምረት የሚያስችል ፋብሪካ በደንበጫ ወረዳ ለመገንባት እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ይፋ አድርጓል።

ሆኖም በክልልም ሆነ በከተማ ደረጃ ለዚህ አይነት ፋብሪካ ፍቃድ እንዳልተሰጠ የክልሉ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ያስታወቀ ሲሆን፥ ፍቃድ የሰጠ አካል ካለም በአፋጣኝ እንዲመልስ አሳስቧል።

FBC

Share.

About Author

Leave A Reply