በአዲስ አበባ ሲሰጥ የነበረው የመታወቂያ አገልግሎት በጊዜያዊነት መቆሙን አስተዳደሩ ገለፀ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ 119 የወረዳ አስተዳደሮች ሲሰጥ የቆየው የመታወቂያ አገልግሎት በጊዜያዊነት መቆሙን የከተማ አስተዳደሩ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጄንሲ አስታወቀ።

ኤጄንሲው ጉዳዩን በተመለከተም በነገው ዕለት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጥ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አስታውቋል።

መታወቂያ መስጠት በጊዜያዊነት እንዲቆም የተወሰነው በአገልግሎት አሰጣት ላይ የሚታዩ ችግሮችን መቅረፍ እንዲቻል መሆኑን ኤጄንሲው ገልጿል።

በተቀመጠው የአገልግሎት መመሪያን ተላልፈው ባለጉዳዮችን የሚያስተናግዱ ተቋማት መኖራቸው የተገለፀ ሲሆን፥ በዚህ ተግባር የተሰማሩ አካላትም ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አስተዳደሩ አሳስቧል።

Share.

About Author

Leave A Reply