በኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋ የወዳጅ ዘመዳቸውን አስከሬን ያጡ ኬኒያውያን የእንጨት ጉማጅ ሊቀብሩ ነው

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

በለፈው ሳምንት እሁድ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ አውሮፕላን ላይ በደረሰው አደጋ ወዳጅ ዘመዶቻቸውን ያጡና አስከሬናቸውን አይተው ሀዘናቸውን መቁረጥ ያልቻሉ ኬኒያውያን የእንጨት ጉማጅ ሊቀብሩ ነው።

ኬኒያውያኑ አዲስ አበባ ድረስ በመምጣት የወዳጅ ዘመዶቻቸውን አስከሬን ማግኘት ሳይችሉ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል። በዚህም ምክኒያት እርማቸውን መውጣት ባለመቻላቸው ሀዘናቸው እጥፍ ድርብ እንደ ሆነባቸው ነው የሀገሪቱ ተነባቢ ጋዜጣ ዛሬ የዘገበው።

ሳተርደይ ኔሽን የተሰኘው ይሄው ጋዜጣ እንዳለው ኬኒያውያኑ ሀዘናቸውን ለመወጣት የእንጨት ጉማጅ የሚቀብሩ ሲሆን ከዚህም ጋር እንሣትን በማረድና በመቅበር የዘመዶቻቸውን ሀዘን ለመውጣት ማቀዳቸውን ዘግቧል።

በዚሁ አደጋ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች አስከሬን ሙሉ በሙሉ ለመለየት አለመቻሉንና ይህንንም ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ለመስጠት መቸገሩን አየር መንገዱ መግለጹ ይታወቃል።

ቃሊቲ ፕሬስ

Share.

About Author

Leave A Reply